" በክፍለ ከተማው በስነ ምግባር የታነጸና በስፖርት የዳበረ ዜጋን ማፍራት የሚያስችሉ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ግንባታ ተጠናክሮ ይቀጥላል ። " ፦ አቶ ወልዴ ወገሴ
በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 አስተዳደር በህብረተሰቡ ተሳትፎ የሚገነባ ሁለገብ የስፖርት ማዝወተሪያ ስፍራ የመሰረተ ድንጋይ ተቀመጠ።
በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ ወገሴ እንደተናገሩት አስተዳደሩ የማህበረሰቡን ሁለንተናዊ እድገትና ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ስኬታማ ስራዎች ማከናወኑን ተናግረዋል፡፡
መንግስት የማህበረሰቡን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ ከሚሰራባቸው ዘርፎች ውስጥ አንዱ ስፖርት መሆኑን በማንሳት በስነ ምግባር የታነፀ፣ ሀገሩን የሚወድና በስፖርት የዳበረ ዜጋ ለእድገትና ለብልፅግና ቁልፍ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በስነ ምግባር የታነጸና በስፖርት የዳበረ ዜጋ ማፍራት የሚያስችሉ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ግንባታ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸው ህብረተሰቡ ለዘርፉ እያደረገ ያለውን ድጋፍ የሚደነቅ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰለሞን ታደሰ ስፖርት ለአካልም ሆነ ለአዕምሮ ጤና የማይተካ ሚና እንዳለው በመጥቀስ ማህበራዊ መስተጋብራችንንም የሚያጠነክር በመሆኑ ነዋሪዎች ያላቸውን ሃበትና ጉልበት በማስተባበር ለዘርፉ ያደረጋችሁት ተግባር ለሌሎች አርዓያ የሚሆን ነው ብለዋል።