የጉለሌ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት የ13ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባዔውን ማካሄድ ጀምሯል።

user 23-Jul-2026 ልማት

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት የ13ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባዔውን ማካሄድ ጀምሯል።

በጉባዔው መክፈቻ ላይ የክፍለ ከተማው ዋና ሥራ አስፈፃሚ  አቶ ወልዴ ወገሴ የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን፤ በበጀት ዓመቱ በሰው ተኮር ኢኒሼቲቮች፣ በአገልግሎት አሰጣጥ፣ በተቋም ግንባታ፣ በሰላምና ጸጥታ እንዲሁም በማህበራዊና ኢኮኖሚ ዘርፎች አበራች ስኬቶች መመዝገባቸውን ገልጸዋል።

በሪፖርቱ ከተጠቀሱ ዋና ዋና ስኬቶች መካከል፦
1.ሰላምና ጸጥታ፦ ህብረተሰቡን በንቃት በማሳተፍ አስተማማኝና ፍጹም ሰላማዊ አካባቢ መፍጠር ተችሏል።
2.የሥራ ዕድልና ኢኮኖሚ፦38,210 ወጣቶችና ሴቶች የሥራ ዕድል የተፈጠረ ሲሆን፤ የሰንበቴ ገበያዎችን ተደራሽ በማድረግ የኑሮ ጫናን ለማቃለል ተሰርቷል።

3.ሰው ተኮር ኢኒሼቲቮች፦ የአቅመ ደካሞችን ቤቶች የማደስ እና የማዕድ ማጋራት መርሃ-ግብሮች በስፋት ተከናውነዋል።
4.ዲጂታላይዜሽንና ማህበራዊ ዘርፍ፦ የአገልግሎት አሰጣጡን ዲጂታል በማድረግ የተገልጋይ እርካታን ማሳደግ የተቻለ ሲሆን፤ በትምህርትና ጤና ተደራሽነትና ጥራት ላይም ውጤታማ ሥራዎች ተከናውነዋል።

የቀጣይ ትኩረት፦
በበጀት ዓመቱ የተገኙ ስኬቶችን በማስቀጠል፣ የኑሮ ውድነትን ማረጋጋት፣ የአገልግሎት አሰጣጥ ቀልጣፋነትን ማሳደግ፣ የተቋማት የአፈጻጸም ልዩነትን ማቀራረብና የልማት ሥራዎችን በመጠበቅ የነዋሪውን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ በቀጣይ ትኩረት የሚሰጣቸው ዋና ዋና ተግባራት መሆናቸው ተመላክቷል።

Related Post

ልዩ ዜና