በክፍለ ከተማው አስተዳደር ባሉ ተቋማት የሚሰጡ አገልግሎት አሰጣጡ ቀልጣፋ በመሆኑ ጊዜያቸውን በአግባቡ መጠቀም መቻላቸውን ተገልጋዮች ገለጹ።

user 05-Aug-2026 ልማት

በክፍለ ከተማው አስተዳደር ባሉ ተቋማት የሚሰጡ አገልግሎት አሰጣጡ ቀልጣፋ በመሆኑ ጊዜያቸውን በአግባቡ መጠቀም መቻላቸውን ተገልጋዮች ገለጹ።

​በቤቶች ልማት አስተዳደር ጽ/ቤት አገልግሎት ያገኘናት ወ/ሮ አለምነሽ አማረ በተቋሙ የሚሰጠው አገልግሎት ግልጽ፣ ቀልጣፋና ውጤታማ ነው ብለዋል።

ባለሙያዎች ከበር ጀምሮ የት መሄድና መገልገል እንዳለባቸው መረጃ እንደሚሰጧቸው ጠቁመው አገልግሎቱ በዚሁ ሊቀጥል እንደሚገም ተናግረዋል።

​ሌላኛዋ በጽህፈት ቤቱ የውል ማስረጃ ለማግኘት የመጡት ተገልጋይ አቶ ተክሉ ሙሉጌታ በበኩላቸው፣ የአገልግሎት አሰጣጡ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መምጣቱን ገልጸዋል።

በመሆኑም ያላስፈላጊ ምልልስና እንግልት ሳይገጥማቸው ለያዙት ጉዳይ ቀጥተኛ ምላሽ ማግኘት መቻላቸውን በደስታ ተናግረዋል።

በመስሪያ ቦታዎችና ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት ያገኘናቸው ተገልጋይ ወ/ሪት ሃሊማ ሲራጅ በአገኘቺው አገልግሎት መደሰታቸውን ተናግረው ያለ አስፈላጊ ምልልስ ሳያደርጉ የመስሪያ ቦታ ውል እንዳደሱ ገልጸዋል።

​የባለጉዳይ ቀናትን ምክንያት በማድረግ የሚደረገው ምልከታ በተጠናከረ መልኩ ተጠናክሮ ይቀጥላል።

Related Post

ልዩ ዜና