የጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር "ሰብዓዊ ድጋፍ በራስ አቅም" በሚል መሪ ቃል ልመናና ተረጂነትን ማስቀረት በሚቻልበት ዙሪያ ከ10ሩም ወረዳ ከተወጣጡ ነዋሪዎች ጋር ውይይት ተካሂዷል።
ውይይቱን የመሩት የጉለሌ ክፍለ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ይከበር ስማቸው እንደተናገሩት ከለውጡ ማግስት እየሰራን ባለው ስራ ከጥገኝነትና ከተረጅነት ስሜት ተላቀን በራሳችን መቆም የምንችልበትን እድል የሚፈጥሩ ውጤታማ ስራዎችን እየተሰራ መሆኑን በመግለጽ አደጋዎች በሚከሰቱበት ወቅት ፈጣን የሰብዓዊ ድጋፍ ማድረግ እንዲቻል እቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑንና ሁሉም አካል እንደ ዜጋ የሚጠበቅበትን ተግባር መወጣት እንደሚኖርበት ተናግረዋል።
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚና ስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰለሞን ታደሰ በበኩላቸው ተረጂነትንና ልመናን በዘላቂነት ማስቀረት የክብራችንና የሉዓላዊነታችን ጉዳይ እንደሆነ በመረዳት በክፍለ ከተማችን የተጀመረው የምግብና የሰብዓዊ ድጋፍ ሉዓላዊነትን በራስ አቅም የማረጋገጥ እንቅስቃሴ ውጤታማ የሚሆነው ሁሉም በአስተሳሰብ ወደ ምርታማነት ሲሸጋገርና ያለንን አቅም አቀናጅቶ መጠቀም እንደሚገባ ተናግረዋል።
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ምክትልና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ገነት ዋቅጋሪ በበኩላቸው ተረጅነትን ለማስቀረት በመንግስት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት ምርታማነትን በማሳደግ ከድህነት ለመውጣት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመው አደጋን ቀድሞ መከላከል ተቀዳሚ ተግባራችን ቢሆንም አደጋዎች ከቁጥጥር ውጭ በሚሆኑበት ወቅት የከፋ ሰብዓዊ ቀውስ ሳያስከትሉ በራሳችን አቅም ፈጣን ምላሽ መስጠት የምንችልበትን እድል የሚፈጥር በመሆኑ የተጀመረው እንቅስቃሴ ይበልጥ ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል ብለዋል።