የጉለሌ ክፍለ ፋይናንስ ጽ/ቤት ፣ የክፍለ ከተማው ንግድ ጽ/ቤት እና የክፍለ ከተማው አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት፣ “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ቃል የተጀመረውን የ2018/2019 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር በዛሬው ዕለት አካሂደዋል።
በንቅናቄው ላይ በርካታ ቁጥር ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች የተሳተፉ ሲሆን ችግኞችን በመትከል የበኩላቸውን አሻራ አኑረዋል።
በማስጀመሪያ መርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የጉለሌ ክፍለ ከተማ ፋይናንስ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ እንየው ሃይሉ ለተሳታፊዎቹ ባደረጉት ንግግር፥ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የአካባቢን ስነ-ምህዳር ከመጠበቅ ባለፈ ለምግብ ዋስትና እና ለስራ ዕድል ፈጠራ ያለውን ዘላቂ ጠቀሜታ አብራርተዋል።
“ይህ ‘ተስፋን እንትከል’ በሚል መሪ ቃል የጀመርነው የ2018/2019 የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር፥ ዛሬ የምንቆፍረው እያንዳንዱ ጉድጓድና የምንተክለው እያንዳንዱ ችግኝ የነገውን ለምለምና ምርታማ አካባቢ የምናረጋግጥበት መሰረት ነው። በዚህ ሀገራዊ ጥሪ ላይ በግንባር ቀደምትነት በመሳተፍ እያሳያችሁት ያለው ተነሳሽነትና ጉልበት በእጅጉ የሚደነቅ ነው ብለዋል።
የክፍለ ከተማው አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሃና ምህረቱ የተተከሉትን ችግኞች ከመትከል ባለፈ ተንከባክቦ ማሳደግና ለውጤት ማብቃት የሁሉንም አካላት የተቀናጀ ክትትል እንደሚጠይቅ አሳስበዋል።
ተጠቃሚዎች የነገዋን ሀገር በልማት ለመገንባት ያላቸውን ቁርጠኝነት ባሳዩበት ከፍተኛ የህዝብ ተሳትፎ በስኬት ተጠናቋል።