" ውብ ፣ ጽዱና ማራኪ የተቀናጀ ሞዴል ብሎኮችን ለጤናችንና ለነዋሪዎቻችን !! "

user 17-Jul-2026 መዝናኛ

" ውብ ፣ ጽዱና ማራኪ የተቀናጀ ሞዴል ብሎኮችን ለጤናችንና ለነዋሪዎቻችን !! "

በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 አስተዳደር የተቀናጀ ሞዴል ብሎክ ምርቃትና ከነዋሪዎች ጋር የርክክብ መርሃ ግብር ተካሄደ።

በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ ወገሴ እንደተናገሩት በክፍለ ከተማው ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በርካታ ሰው ተኮር የልማት ስራዎች በማከናወን ላይ ሲሆን በዚህም የነዋሪውን መሠረታዊ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ ከማድረግ ባለፈ የህብረተሰባችንን የኑሮ ደረጃውን ለማሳደግ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

ዋና ስራ አስፈጻሚው አክለውም ከነዚህ ተግባራት መካከል ህብረተሰቡ አካባቢውን በማስዋብ ለኑሮ ምቹ ውብና ተስማሚ በማድረግ ሞዴል አካባቢን በመፍጠር በመስራት አርዓያ የሚሆን ተግባር እያከናወነ ሲሆን ለዚህ ማሳያ በዛሬው ዕለት የተመረቀው በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 አስተዳደር የተቀናጀ ሞዴል ብሎክ ለዚህ ማሳያ ነው ብለዋል።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሽመልስ ጎዴቦ በበኩላቸው በክፍለ ከተማው የነዋሪውን ሁለንተናዊ ልማትና ብልጽግና የሚያረጋግጡ ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛል ከነዚህም አንዱ ሞዴል አካባቢ ፣ ሞዴል መንደርና ሞዴል ቤተሰብ በመፍጠር ነዋሪዎች ጤናማ በሆነ አካባቢ የመኖር መብታቸው በመሆኑ ሁሉም ለልማቱ ንቁ ተሳትፎ ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል።

በቀጣይም ማህረሰቡ የሚኖርበትን ብሎክ የተሟላ፣ ለህፃናት ምቹና ዘመናዊ መጫወቻ ያለዉ እንዲሆን በማልማት፣ በማፅዳት፣ በማስዋብ፣ ሠላማዊ ከባቢ በመፍጠር፣ ክ/ከተማዋ ብሎም መዲናችን አዲስ አበባ ለመኖርያ ምቹና ተመራጭ እንድትሆን ቀጣይንነት ባለዉ መልኩ ማልማት ያስፈልጋል ብለዋል።

Related Post

ልዩ ዜና