የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤ

user 06-Feb-2026 ማህበራዊ ጉዳዮች

በ2018 በጀት ዓመት የ 6 ወር እቅድ አፈፃፀማችን በአማካይ 95.3% ማሳካት ችለናል፡፡" ከንቲባ አዳነች አቤቤ

በመዲናችን አዲስ አበባ በ2018 በጀት ዓመት በ6 ወራት ዉስጥ በሁሉም ዘርፎች በ24/7 የስራ መርህ በተሰራዉ ስራ በአማካይ 95.3% ማሳካት ችለናል ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ በአቀረቡት ሪፖርት ገልፀዋል፡፡

ሰላም እና ፀጥታ በተመለከተ

የበዓላት አከባበር ላይ ከነዋሪዎች፣ ከሃይማኖት ተቋማትና ከጸጥታ አካላት ጋር በተደረገ ቅንጅት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ታዳሚዎች የተሳተፉባቸው የአደባባይ በዓላት (ሃይማኖታዊ፣ ባህላዊና ሕዝባዊ) ያለምንም የጸጥታ ችግር በድምቀት ተከብረዋል።

የሰላም ሰራዊት ተሳትፎ ከማሳደግ አኳያ ከ22 ሺህ በላይ አዳዲስ የሰላም ሰራዊት አባላትን በመመልመልና በማሰልጠን ከጸጥታ ኃይሉ ጋር በመቀናጀት በየቀኑ ለከተማዋ ሰላም አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ተደርጓል።

የደንብ ማስከበርና የሕገ-ወጥነት መከላከል በተመለከተ

በከተማችን የሚስተዋሉ የደንብ መተላለፎችና ህገወጥ ተግባራትን ለመከላከል ፣ ለመቆጣጠርና ተፈፅሞም ሲገኝ ማረም እንዲቻል ብቁ በስነምግባር የታነጹ የደንብ ማስከበር ኦፊሰሮችን በ9 ዙሮች በማሰልጠን በስነ-ምግባር የታነጹ የደንብ ማስከበር ኦፊሰሮች ሰልጥነው ወደ ሥራ ገብተዋል።

የደንብ መተላለፍ ቁጥጥር ላይ በመሬት ወረራ፣ በሕገ-ወጥ ግንባታ፣ በጎዳና ንግድ፣ በሕገ-ወጥ እርድና ማስታወቂያ፣ እንዲሁም በደረቅና ፍሳሽ አወጋገድ ዙሪያ የሚታዩ ሕገ-ወጥ ተግባራትን የመከላከልና የማረም ሥራ ተከናውኗል።

አዋኪ ድርጊቶች፤ ህገ-ወጥ የመንገድ አጠቃቀም በመከላከል ረገድ አበረታች ስራ ተከናዉኗል።

የፍትሕ ሥርዓት ማስከበር በተመለከተ

የወንጀል ምጣኔ ከመቀነስ አኳያ ከህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር፤ ከህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር፣ ከዝርፊያና፣ ደረቅ ወንጀሎች ጋር የተያያዙ በርካታ እርምጃዎች የመውሰድ ስራ ተሰርቷል፡፡

በፍትሀብሔር ጉዳዮች የከተማ አስተዳደሩንና የነዋሪውን መብትና ጥቅም ከማስጠበቅ አንፃር በፍርድ ቤት ክርክር የቀረቡ 4,140 መዝገቦች ውስጥ በፍ/ቤት ውሳኔ ካገኙ 1,491 መዝገቦች 1,382 ለአስተዳደሩ ማስወሰን በመቻሉ ማስከበር የተቻለ የመንግስት እና ሕዝብ መብትና ጥቅም በገንዘብ 3 ቢሊዬን ብር በላይ ሲሆን፣ በአይነት ደግሞ 101 ቤቶች፣ 19 ሼዶች እንዲሁም 178.62 ሄክታር መሬት ህጋዊነት ማስከበር ተችሏል፡፡ከንቲባ

የትምህርት ዘርፍ በተመለከተ

የከተማ አስተዳደሩ ባለፉት የለውጥ አመታት ለትምህርት ዘርፉ ልዩ ትኩረት በመስጠት ባደረገው ከፍተኛ ኢንቨስትመንት መሰረት አበረታች ውጤቶች የተመዘገቡ ሲሆን በበጀት ዓመቱ በ 6 ወራት በተሰራዉ ስራ

ከተማሪዎች ውጤት አንጻር፤ የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና 50% በላይ ያመጡ ተማሪዎች 2015 ዓ.ም ከነበረበት 80.2% በአሁን ወቅት 95% ማድረስ ተችሏል::

የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና 50% በላይ ያመጡ ተማሪዎች 2010 ዓ.ም ከነበረበት 36.1% በአሁን ወቅት ወደ 88.8% ከፍ ብሏል።

12ኛ ክፍል ሃገር አቀፍ ፈተና 50% በላይ ያመጡ ተማሪዎች 2013 ዓ.ም ከነበረበት 25.45% በአሁን ወቅት 31% ከፍ ማለቱ እና በመንግስትና በግል ትምህርት ቤቶች መካከል የነበረውን የውጤት ልዩነት በከፍተኛ ደረጃ ተቀራራቢ የአፈጻጸም ውጤት እንዲመዘገብ አስችሏል፡፡

የትምህርት ተሣትፎና ፍትሐዊነት በማሳደግ በዕውቀትና በሥነ- ምግባር የታነፀ ትውልድን ለማፍራት ከቅድመ አንደኛ ደረጃ እስከ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት አጠቃላይ ተማሪ ቅበላ ከነበረበት 1,253,737 ወደ 1,334,830 የደረሰ ሲሆን ካለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የተማሪ ቁጥር 81,093 ዕድገት አሳይቷል።

የትምህርት ፍትሃዊነትና አካታችነትን ለማስፈን በተደረገው ጥረት በሁሉም ት/ቤቶች የልዩ ፍላጎት ትምህርትን በማስፋፋት በጥቅሉ 124 ማእከላትን ማድረስ ተችሏል፡፡

በ80 ት/ቤቶች ራምፕ ጥገና እና ራምፕ በሌላቸው 4 ት/ቤቶች በአዲስ መልክ የመገንባት ሥራ ፤ ለአይነ ስውራን ተማሪዎች የብሬል መፅሃፍ ህትመት በማከናወን ስራ እንዲሁም ለ36 ትምህርት ቤቶች ለተማሪዎች እና ለመምህራኑ ስፈላጊ ሆኑ ግበዓቶች እንዲሟሉ ተደርጓል::

የት/ቤቶችን መሠረተ ልማት ለማሻሻል ባለፉት 6 ወራት “ትምህርት ለትውልድ” ንቅናቄ በተሰራው ሥራ ተለያዩ ባለድርሻ አጋር አካላትን በትምህርት ጥራት ላይ ተሳትፎአቸዉን በማጠናከር በጥሬ ገንዘብ 637,253,857፤ በዓይነት 1,137, 493,918፤ በጉልበት 211,388,874፣በዕቀውት 243,478,637 በድምሩ 1.32 ቢሊየን ለመሰብሰብ ታቅዶ ክንውን 2.23 ቢሊየን (100% በላይ) ሀብት ማሰባሰብ ተችሏል፡፡

በተማሪዎች ምገባ፤- በቅድመ አንደኛ እና አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ላይ 940,329 በላይ ተማሪዎች በቀን ሁለት ጊዜ እንዲመገቡ እየተደረገ ሲሆን የተማሪ ዩኒፎርም፣ የትምህርት ቁሳቁስ እና የመምህራን ጋዋን በወቅቱ እንዲደርሳቸው በማድረግ በኢኮኖሚያዊ ጫና ምክንያት ትምህርታቸውን የሚያቋርጡ ተማሪዎች (መጠነ ማቋረጥ)፤የሚደግሙ (ተማሪዎች መጠነ መድገም) ጉልህ በሆነ መልኩ መቀነስ እንዲሁም በተማሪዎች መካከል የእኩልነት ስሜት በማዳበር የስነ ልቦና ጫናን መቀነስ ተችሏል፡፡

ባለፉት 6 ወራት በንግዱ ዘርፍ የተመዘገቡ ዋና ዋና ስኬቶች በተመለከተ

የገበያ መረጋጋት እና የምርት አቅርቦት

 

የሰብል አቅርቦት 688,153 ኩንታል በላይ ፤

 

 

አትክልትና ፍራፍሬ 3,899,375 በላይ ፤

 

 

ዳልጋ ክብት እና በግና ፍየል 2,127,208 በላይ ማቅረብ የተቻለ ሲሆን፤

 

 

በተጨማሪም የድጐማ ምርቶች በተለይ በየቀኑ በሚሊዮኖች የዳቦ አቅርቦትን በመጨመር፣

 

 

12,601,755 ሊትር የምግብ ዘይትና 242,892 ኩንታል ስኳር በማቅረብ የከተማችንን ነዋሪዎች የኑሮ ጫና የሚያቃልሉ ተጨባጭ ስራዎች አከናውነናል ፡፡

 

 

የንግድ መሠረተ ልማት እና ቁጥጥር

 

የደላላን ሰንሰለት ለመበጠስና ሸማቹን ከአምራች ጋር በቀጥታ ለማገናኘት ሰፊ ስራዎች ተሰርተዋል፦

 

የገበያ ማዕከላት፦ በአምስቱም የከተማ መግቢያዎች ከተገነቡት በተጨማሪ የላፍቶ ቁጥር 2 ገበያ ማዕከል ወደ አገልግሎት ገብቷል።

 

 

የቅዳሜና እሁድ ገበያ፦ የገበያ ቦታዎች ቁጥር ከ219 ወደ 245 ከፍ እንዲል ተደርጓል።

 

 

ህጋዊነትን ማስፈን፦ በ230,013 ድርጅቶች ላይ ክትትል ተደርጎ፣ 12,139 ጥፋተኞች ተለይተዋል። ከእነዚህም ውስጥ 10,496 ነጋዴዎች ወደ ህጋዊ መስመር ተመልሰዋል።

 

 

መደበኛ ያልሆነ ንግድ፦ 7,400 መደበኛ ያልሆኑ አነስተኛ ንግዶችን ህጋዊ እውቅና በመስጠት ወደ ስራ እንዲገቡ ተደርጓል።

 

ባለፉት 6 ወራት በጤናው ዘርፍ የተመዘገቡ ዋና ዋና ስኬቶች ባጭሩ፦

1. የጤና ጥራትና ዲጂታላይዜሽን

 

የሞት ምጣኔ፦ የእናቶችና የጨቅላ ህጻናት ሞትን በመቀነስ የ2030 የዘላቂ ልማት ግቦች (SDGs) ተሳክተዋል።

 

 

ወረቀት አልባ አገልግሎት፦ ሁሉም ሆስፒታሎችን ጨምሮ 67 የጤና ተቋማት የኤሌክትሮኒክ መረጃ አያያዝ (EMR) መተግበር ጀምረዋል።

 

2. የጤና መድህንና ተደራሽነት

 

ተጠቃሚነት፦ 2.7 ሚሊዮን አባላት ያሉት ሲሆን፣ 1.49 ሚሊዮን ዜጎች በጤና መድህኑ ታክመዋል።

 

ድጋፍ፦ መንግስት በዓመት ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት ይመድባል።

3. መሰረተ ልማትና ሆስፒታሎች

 

አዳዲስ ተቋማት፦ 9 አዲስ ጤና ጣቢያዎች ተገንብተዋል፤ 13ቱ ላይ የማስፋፊያ ስራ ተሰርቷል።

 

ግዙፍ ፕሮጀክቶች፦ የኮልፌ መንዲዳ፣ የንፋስ ስልክ ላፍቶ እና የገላን ትራውማ ሆስፒታሎች ግንባታ ተጠናቆ ወደ ስራ ለመግባት ተዘጋጅተዋል።

 

ራስን መቻል፦ ሁሉም ሆስፒታሎች የራሳቸው የኦክስጅን ማምረቻ እንዲኖራቸው ተደርጓል።

 

4. የህጻናት ልማትና አልሚ ምግብ

 

እንክብካቤ፦ 1.3 ሚሊዮን ህጻናትን ታሳቢ ያደረገ ፕሮግራም ተቀርጿል፤ 1,000 ማቆያዎች ተገንብተዋል።

 

 

በካሳንቺስ 5 ሄክታር ላይ "የህጻናት አለም" እየተገነባ ነው።

 

 

አካላዊ እድገት ውስኑነት ለታየባቸው 185 ህጻናት ችግራቸውን ታሳቢ ያደረግ የዊልቼር ድጋፍ ተደርጓል።

 

 

ምክርና ድጋፍ፦ ለ245,803 ቤተሰቦች የቤት ለቤት ምክር ተሰጥቷል፤ ለ15,000 እናቶችና ህጻናት የአልሚ ምግብ ድጋፍ ተደርጓል።

 

 

ውጤት፦ የህጻናት እድገት ሁኔታ 2.7% መሻሻል አሳይቷል።

 

ቱሪዝም በተመለከተ

የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት የቱሪዝም ኢንዱስትሪው ለከተማዋ ዕድገት ያለውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አስተዋፆኦ ለማሳደግ በርካታ የቱሪዝም መዳረሻዎች እንዲለሙ ተደርጓል፡፡

በዚህም ወደ ከተማችን የሚመጡ ቱሪስቶች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ በፍጥነት እየጨመረ ይገኛል፡፡

• ባላፉት ስድሰት ወራት ከተማችንን ይጎበኛሉ ተብሎ ከታቀዱ 4.7 ሚሊየን የሀገር ውስጥ ቱሪስቶች 4.9 ሚሊየን ቱሪስቶች መዲናችንን ጎብኝተዋል፡፡

•በከተማችን ላይ ሲከበሩ የነበሩ ህዝባዊ እና ሃይማኖታዊ ባህላዊ የአደባባይ በአላት፤ እንዲሁም የስፖርትና የጤና ቱሪዝም መስፋፋት ከፍተኛ አበርክቶ ነበራቸው፡፡ን መጎብኘት ችለዋል፡፡

ይህም ከባለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃጸር በ15 ፐርሰንት ብልጫ አሳይቷል፡፡ ከተማችንን የኮንፍረንስ ቱሪዝም ማእከል ለማድረግ የተከናወኑ በርካታ የልማት ስራዎችና ሜጋ ፕሮጀክቶች ፍሬ በማፍራት በከተማችን ውስጥ የሚደረጉ ኩነቶች ጨምረዋል፡፡

•ባለፉት ስድት ወራት 150 የሚሆኑ አለማቀፍና አህጉር አቀፍ ኩነቶች አዲስ አበባ ላይ ተካሂደዋል፡፡ ይህም ከባለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃጻር የ50 በመቶ እድገት አሳይቷል፡፡

በአጠቃላይ ከሀገር ውስጥ እንዲሁም

• በተመሳሳይ 699,761 ቱሪስቶች ከተማችንከውጪ ሀገር የቱሪስት ፍሰት ባለፉት ስድት ወራት 155 ቢሊየን ብር ወደ ኢኮኖሚ ፈሰስ ማድረግ ተችሏል፡፡

Related Post

ልዩ ዜና