አዲስ አበባ ባስመዘገበቻቸዉ ስኬቶች በዓለም አቀፍ መድረክ እዉቅና ካገኘችባቸዉ ዋና ዋና ዎቹ፤-
መዲናችን አዲስ አበባ በሁለንተናዊ መልካም ገጽታ በዓለም መድረክ ላይ በግልጽ ያሳዩ የቱሪዝም እና የኢኮኖሚ እድገት ታላላቅ ስኬቶችን አስመዝግባለች ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ፡፡
ከንቲባዋ አክለዉም በሪዮደጀነሪዮ የተቀበለችው የምገባ ኘሮግራም ሽልማት፤በደቡብ ኮሪያ የተበረከተውና ለከተማዋ አመራር እውቅና የሰጠው የሴኡል ስማርት ከተማ ሽልማት (2024) እንዲሁም ለቆሻሻ አወጋገድ ስርዓት መሻሻል በቦነሳረስ የተሰጠው እውቅና “ የC40 ከተሞች የብሉምበርግ ሽልማት ተጠቃሾች ናቸዉ ብለዋል፡፡
አያይዘዉም በናይሮቢ ኬንያ በተካሄደው የአፍሪካ ስማርት ከተሞች ኢንቬስትመንት ሰሚት የተሰጠው የአፍሪካ ምርጥ ስማርት ከተማ ሽልማት (2024) ሲሆን በመንገድ ደህንነትና ፍጥነት ማስተዳደር ላይ ባስመዘገበችው ውጤት በአለም አቀፍ የከተሞች የዘርፉ ውድድር የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ጭምር መሆኗን ተናግረዋል፡፡
በመጨሻም ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በተያያዘ አዲስ አበባ የብሉምበርግ ፊላንትሮፒስ የከተሞች ጥምረት አባል ለመሆን ችላለች ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለምክር ቤት አባላት ባቀረቡት ሪፖረት ገልፀዋል፡፡