የጉለሌ ከተማ ምክር ቤት 13ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባዔ እያካሄደ ይገኛል ::

user 21-Oct-2025 ልማት

የጉለሌ ከተማ ምክር ቤት 13ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባዔ እያካሄደ ይገኛል :: በምክር ቤት አባላት ከተነሱ ጥያቄዎች መካከል፦

በጉባኤው የምክር ቤት የመራጭ ተመራጭና የቋሚ ኮሜቴ አባላቱ ከመረጣቸው ህዝብ ጋር ባደረጉት ውይይት ምላሽና ማብራሪያ ያስፈልጋቸዋል ተብለው የተነሱት ጥያቄዎች ዋና ዋናዎቹ ፡-

? የወጣቶች የስራ ዕድል ተጠቃሚነት የመስሪያ ቦታዎች ከማስተላለፍ አንጻር

? ከኑሮ ዉድነት ከማረጋጋት አንጻር የሸማቾች የፍጆታ ምርቶች በቂ አቅርቦት አለመኖር

? ከመሠረተ ልማት ስራዎች የውሃና የመብራት መቆራረጥና መጥፋት በተመለከተ

?የአገልግሎት አሰጣጥ የትራንስፖርት አቅርቦት ችግር

? የሠላምና ፀጥታ ስራዎች የዘረፋና አዋኪ ድርጊቶች መቅረፍ

? የመልካም አስተዳደር የህዝብ መጸዳጃ በቂ ግንባታ አለመኖር

? የመንግስት ቤቶች አገልግሎት አሰጣጥ በተመለከተ የሚሉ ጥያቄዎች በምክር ቤቱ አባላት የተነሱ ሲሆን ለጥያቆዎቹም በአቶ ወልዴ ወገሴ ምላሽ የሚሰጥ ይሆናል፡፡

Related Post

ልዩ ዜና