የተቋማት ቅንጅታዊ አሰራርን ማጠናከር በሁሉም ዘርፍ ውጤታማ ስራዎችን ለመስራት እንደሚያስችል ተገለፀ።

user 29-Oct-2025 ማህበራዊ ጉዳዮች

የተቋማት ቅንጅታዊ አሰራርን ማጠናከር በሁሉም ዘርፍ ውጤታማ ስራዎችን ለመስራት እንደሚያስችል ተገለፀ።

በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የተቋማት ቅንጅታዊ አሰራርን ማጠናከር በሁሉም ዘርፍ ውጤታማ ስራዎችን ለመስራት እንደሚያስችል ተገለጸ።

የተቋማት ቅንጅታዊ አሰራር በ7 ክላስተር ተደራጅቶ ተግባሩ እንዲመራ በሚያስችል ማኑዋል ላይ የክፍለ ከተማ የክላስተር አስተባባሪ አመራሮች በተገኙበት ውይይት ተደርጓል።

በቀረበው ማኑዋል ላይ የተቋማት የክላስተር ደረጃም ቁልፍ፣ ደጋፊ እና ባለዘርፈ ብዙ ተብለው የተፈረጁ ሲሆን የክላስተሮቹ አደረጃጀት፣ ተግባርና ሃላፊነትም በዝርዝር ቀርቧል።

የክፍለ ከተማው መልካም አስተዳደር ቅሬታና አቤቱታ ጽ /ቤት ኃላፊ አቶ እንደሻው ምንይችል የተቋማት ቅንጅታዊ አሰራር ለውጤታማ ተግባር ወሳኝ መሆኑን ጠቁመው በማኑዋል አተገባበሩ ላይ ለክላስተር አስተባባሪ አመራሮች ስልጠና ሰጥተዋል።

በውይይቱ ላይም የአገልግሎት ጥራትና ተደራሽነት፣ የመልካም አስተዳደር፣ የሃብት አጠቃቀም እና ማዘጋጃ ቤታዊ ስራዎችን በቅንጅት ከመስራት አኳያ ሃሳቦች የተነሱ ሲሆን የክላስተር አስተባባሪዎች በማኑዋሉ ላይ ሃሳብና አስተያየት ሰጥተዋል።

Related Post

ልዩ ዜና