አስተዳደሩ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ተገልጋዮች ገለጹ።

user 11-Jul-2026 ልማት

በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 አስተዳደር የአገልግሎት ቀንን ምክንያት በማድረግ የሚሰጡ አገልግሎቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻሉና ቅልጥፍና እየታየባቸው መምጣቱን ተገልጋዮች ገለጹ።

አስተዳደሩ የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓቱን ለማዘመንና የነዋሪዎችን እንግልት ለመቀነስ እየወሰዳቸው ያሉ እርምጃዎች ውጤት እያሳዩ መሆኑ ተመላክቷል።

ተገልጋዮች በሰጡት አስተያየት ቀደም ሲል ለአንድ ጉዳይ ተደጋጋሚ ቀጠሮ ይሰጠን ነበር አሁን ግን በግልጽ የተቀመጠ መረጃና ፈጣን ምላሽ እያገኘን ነው ሲሉ ነዋሪዎች የአገልግሎት አሰጣጡን በመልካም ደረጃ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

በወረዳው አስተዳደር የባለጉዳይ ቀንን አስመልክቶ ረቡዕ እና አርብ ተገልጋዩን ህብረተሰብ ማገልገሉን ተጠናክሮ ቀጥሏል።

Related Post

ልዩ ዜና