የጉለሌ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት የተለያዩ የማህብረሰብ ክፍሎችን በማስተባበበር 16 የአቅመ ደከማ ቤቶችን በመገንባት አስረክቧል፡፡

user 27-Oct-2025 ማህበራዊ ጉዳዮች

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት የተለያዩ የማህብረሰብ ክፍሎችን በማስተባበበር 16 የአቅመ ደከማ ቤቶችን በመገንባት አስረክቧል፡፡

በቤቶች የርክክብ መርሃግብር ግብር ላይ የአዲስ አበባ ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ክብርት ፈይዛ መሐመድ፣የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ወልዴ ወገሴ፣ የከተማ አስተዳደሩ የምግብ እና መድኃኒት ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሙሉ እመቤት ታደሰ፣ የክፍለ ከተማው ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ መኩሪያ ጉርሙ እና የክፍለ ከተማና የወረዳዎች የምክር ቤት አፈጉባኤዎች ጨምሮ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል፡፡

አዲስ አበባ ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፈይዛ መሐመድ በመርሃ ግብር ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት የከተማ አስተዳደሩ የነዋሪዎችን ህይወት ለማሻሻል በርካታ ሰው ተኮር ተግባራትን ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆንን በማንሳት በክፍለ ከተማው ምክር ቤት አስተባባሪነት የታደሱ የአቅመ ደካሞች ቤቶችን ለተጠቃሚዎች ያስተላለፍነውን በጎ ተግባራት በሌሎችም ተቋማት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ተናግረዋል።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ወልዴ ወገሴ እንደተናገሩት በክፍለ ከተማችን በባለፈው ክረምት ወቅት በህዝቡ እና በበጎ ፍቃደኛ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ትብብር በርካታ ዝቅተኛ የማህብረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ያደረጉ የተለያዩ ሰው ተኮር ተግባራትን ማከናውን መቻሉን በመጥቀስ የዛሬውም የዚሁ ተግባራት አካል በመሆኑ በቀጣይ ለማህበረሰብ ለውጥ በሰው ተኮር ስራችን ላይ ሁላችንም በንቃት መሳተፍ አለብን ብለዋል።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባዔ አቶ መኩሪያ ጉርሙ በበኩላቸው ምክር ቤቱ የአስፈጻሚው አካላት ስራዎች የመከታተልና የመደገፍ ከዋናው ተግባሩ በተጨማሪ መንግስት በሚተገብራቸው የሰው ተኮር ተግባራት ለውጤታማነቱ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን በማስተባበር በዛሬው ዕለት 16 የአቅመ ደካማ ቤቶችን ሙሉ በሙሉ በመገንባት ማስረከብ ተችላል በቀጣይም በሌሎች ሰው ተኮር ተግባራት ላይ በንቃት በመሳተፍ የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት ይሰራል ብለዋል፡፡

ቤት የታደሰላቸው ግለሰቦችም ከዚህ በፊት የነበረውን አመቺ ያልሆነ ኑሮ ቤታቸው ተሻሽሎና አምሮ ተገንብቶ በመረከባቸው ደስተኛ መሆናቸውን በመግለፅ ለከፍለ ከተማው አስተዳደር እና በዚህ ተግባራት ለተሳተፉ በጎ ፍቃደኞች ሁሉም ልባዊ ምስጋናቸውን አቅረበዋል፡፡

Related Post

ልዩ ዜና