የአንድ ማዕከል ሰላም ሰራዊት ስምሪት ተጠናክሮ ቀጥሏል።
(ጉለሌ ኮሙኒኬሽን ፣ 07- 05 -2018 ዓ.ም )
በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 እና ወረዳ 10 አስተዳደር የሰላም ሰራዊት ስምሪት የዘወትር ተግባር ቢሆንም ወቅቱ የጥምቀት በዓል ከመሆኑ ጋር በተያያዘ ከወትሮው የተለየና የተጠናከረ የአንድ ማዕከል ስምሪት እየተሰጠ ይገኛል።
በስምሪቱ ተገኝተው መልእክት ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች፣ ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ እንደገለፁት የክ/ከተማው አስተዳደር ላለፉት በርካታ አመታት ህብረተሰቡን የሰላም ባለቤት አድርጎ በመስራት የአመለካከት የስምሪት ሌሎችንም ስልጠናዎችን በመስጠት አደረጃጀቶችንም በመፍጠር ለጸጥታው አጋዥ እንዲሆኑ በማድረግ አመርቂ ውጤት እንዲመዘገቡ አድርጓል ብለው ለተመዘገበው ውጤትም መላው የክ/ከተማው ነዋሪ ሚናው ሰፊ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የጠላት ሀይል እንቅስቃሴዎች እና ታቅደው የነበሩ ወንጀሎችን በቁጥጥር ስር በማዋልና በመቀነስ የክ/ከተማውን ብሎም የከተማዋን ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ እንደተቻለም ገልጸዋል።
ወ/ሮ ቆንጂት አያይዘውም የሰላም ሰራዊት አባላት የከተማው ሰላም አለኝታ ሆነው እንዲሰሩ፤ የጸጥታውን ስራ ያለ ምንም እንከን አስተማማኝ በማድረግ ከተማዋ እየገሰገሰችበት ካለችው የእድገት ጎዳና አንጻር የሚመጥን ከጸጥታው አካል ጋር ተግባብቶ የሚሰራና በተደራጀ መልኩ መረጃን የሚሰጥ፣ ቴክኖሎጂን የሚጠቀም፣ አካባቢውን ከጸጉረ ልውጥ የሚጠብቅ፣ ሰላምን ለሚያረጋግጠው ህብረተሰብ የሰላም ደሴት መፍጠር የሚችል የሰላም ሰራዊት መሆን እንደሚገባቸው አሳስበዋል ።
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ በበኩላቸው የሰላም ሰራዊት አባላት በፍጹም ዲሲፕሊን የሚመሩ፣ የሀገር ፍቅር ስሜት ያላቸው፣ ለተልዕኮ በዘላቂነት የሚወጡ፣ ለጸጥታ አካላት አጋዥ የሆኑ፣ ጸጉረ ልውጦችን እና ጸረ-ሰላም ሀይሎችን የሚመክት ከጸጥታ ሀይሉና ከማህበረሰቡ ጋር በመቀናጅት የአካባቢውን ሰላምና ደህንነት በንቃት የሚጠበቅ መሆን እንዳለበት እና ይኸንንም በተግባር ማረጋገጡ አበረታች መሆኑን ገልጸዋል ።