የቀዳማይ ልጅነት ግንዛቤን በማስፋት ወጣቶች ራዕይ ያለውና ባለ ብሩህ አዕምሮ እንዲሆኑ ማድረግ እንደሚገባ ተገለጸ።

user 19-Dec-2025 ማህበራዊ ጉዳዮች

የቀዳማይ ልጅነት ግንዛቤን በማስፋት ወጣቶች ራዕይ ያለውና ባለ ብሩህ አዕምሮ እንዲሆኑ ማድረግ እንደሚገባ ተገለጸ።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ስራና ክህሎት ጽ/ቤት የ2018 የእንጠያየቅ መድረክና የቀዳማይ ልጅነት ፕሮግራም ግንዛቤ እንዲሁም የአገልግሎት አሰጣጥና መልካም አስተዳደር ዙሪያ ውይይት አካሄዷል።

በመድረኩ ላይ የተገኙት የጉለሌ ክፍለ ከተማ ስራና ክህሎት ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ መሠረት በለጠ እንደተናገሩት መድረኩ በዘርፉ የሚያጋጥሙ ችግሮችን በተደራጀና በተቀናጀ ሁኔታ መፍትሄ ለመስጠትና ጥራት ያለውን ምርት ለማምረት የሚያስችል መሆኑ ገልጸው በዘርፉ አምራቾች ጠንካራ ግንኙነት በመፍጠር የእርስ በእርስ የልምድ ልውውጥ ለማድረግ የማህበራትን እኩል ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

በመድረኩ ላይ ከአምራቾችና ከባለድርሻ አካላት የተነሱ ጥያቄዎች በዘርፉ ያሉ ቡድኖች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል።

Related Post

ልዩ ዜና