በንግድ ዘርፍ የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞችና አንቀሳቃሾች የሚያጋጥማቸውን ችግሮች ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በመፍታት ውጤታማ እንዲሆኑ ማስቻል እንደሚገባ ተገለጸ።
በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በ10ሩም ወረዳ የስራና ክህሎት ጽ/ቤት አዘጋጅነት " የኢንተርኘራይዞች ውጤታማነት ለአዲስ አበባ ብልጽግና " በሚል መሪ ቃል በንግድ ዘርፍ የነባር ኢንተርፕራይዞች የድጋፍ ማዕቀፍና የባለድርሻ አካላትን ሚና ያካተተ በክፍለ ከተማው የውይይት መድረክ ተካሄደ ።
የጉለሌ ክፍለ ከተማ የስራና ክህሎት ጽ/ቤት በንግድ ዘርፍ ኢንተርፕራይዞች እና አንቀሳቃሾች ጋር የሚያጋጥሟቸውን ማነቆች ለመለየትና ለመፍታት እንዲያስችል ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሄደ።
የውይይቱ ዓላማ በንግድ ዘርፍ ኢንተርፕራይዞች የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች ለመፍታት ባለድርሻ አካላት ተቀናጅቶ በመስራት ምርታማነታቸውን እንዲያረጋግጡ ማስቻል እንደሆ ተገልጿል።
የመድረኩ ላይ ላይ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰለሞን ታደሰ በክፍለ ከተማው በንግድ ዘርፍ ከነባር ኢንተርፕራይዞች ጋር የተካሄደውን መድረክ የነባር ኢንተርፕራይዞችን አቅም ለማጠናከር ምርታማነታቸውን ለማሳደግ የሚገጥሟቸውን የተለያዩ የመልካም አስተዳደር እና የውስጥ ችግሮች ለይቶ ለመፍታት የተደረገ ውይይት መሆኑን ገልፀዋል ።
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ስራና ክህሎት ምክትል ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መሠረት በለጠ እንደተናገሩት በንግድ ዘርፍ ኢንተርፕራይዞች የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በጋራ በመፍታት በቀጣይ ለሚሰሩት ስራ አቅም ከዚህ በፊት የተሰሩ ተሞክሮችን በማድረግ ኢንተርፕራይዞችን ምርትና ምርታማነታቸውን እንዲያረጋግጡ ለማድረግ ያለመ እንደሆነ ገልጸዋል።
ከተሳታፊዎች ሃሳብና አስተያየቶች ሰፊና ጥልቀት ያለው ውይይት የተደረገ ሲሆን ምላሽ ማብራሪያ ተሰጥቶ የጋራ መግባባት በመፍጠር ተጠናቋል