" ህገ-ወጥ እና ኢ-መደበኛ ፍልሰትን በጋራ እንከላከል"

user 05-Jun-2025 ልማት

" ህገ-ወጥ እና ኢ-መደበኛ ፍልሰትን በጋራ እንከላከል"

‎በሰው መነገድ ሰውን በህገ ወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር እና በህገ ወጥ መንገድ ወደ ውጪ መላክ ወንጀል መከላከልና መቆጣጠር ምክር ቤት 3ኛ መደበኛ ጉባኤ በክፍለ ከተማ ደረጃ ተካሄደ።

‎በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በሰው መነገድ በህገ ወጥ መንገድ ድንበር የማሻገርና በህገ ወጥ መንገድ ሰውን ለስራ ከሀገር ውጪ መላክ ወንጀል መከላከል እና መቆጣጠር ምክር ቤት 3ኛ መደበኛ ጉባዔውን አካሄደ።

‎በጉባዔው ላይ በቀረበው ሰነድ ህገ- ወጥ የሰዎች ዝውውር በሀገር ላይ በማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊና ፣ ፖለቲካዊ ችግሮች የሚያስከትል በመሆኑ ሁሉም ባለድርሻ አካላት መወጣት እንደሚገባና በሰዎች የመነገድ እና በህገ ወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣው አዋጅ ቁጥር 1178/2012 ላይ ያለውን ግንዛቤ ላይ በሰፊው መሰራት እንዳለበት ተገልጿል።

‎በመድረኩ ላይ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊና የምክር ቤቱ ሰብሳቢ አቶ ሰለሞን ታደሰ እንደተናገሩት ምክር ቤቱ የተቋቋመበት ዋና ዓላማ ወጣቶችና ሴቶች በህገ ወጥ መንገድ ወደ ውጪ ሀገር በመሄድ የሚደርሰውን የህይወት መጥፋትና ጉልበት ብዝበዛ ለማስቀረት እንደሆነ ተናግረዋል።

Related Post

ልዩ ዜና