በባለጉዳይ ቀን የአገልግሎት አሰጣጥ ምልከታ በጉለሌ ክፍለ ከተማ
(ጉለሌ ኮሙኒኬሽን 21/02/2018)
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት፣የክፍለ ከተማው ብልጽግና ፓርቲ እና የኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት በቅንጅት የተቋማት በባለጉዳይ ቀን የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደትን ምልከታ አድርገዋል፡፡
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፀኃፊ አቶ አብራሃም ምስጋናው፣ የክፍለ ከተማው ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ተወካይ አቶ ደረጃ ክንፈ እና እና የክፍለ ከተማው የኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ሃላፊ ወ/ሮ ሰርካለም ተፈሪ በገራ በመሆኑ የባለጉዳይ ቀንን በማስመልከት ባደረጉት ምልከታ በቀጣይም የተቋማት ኃላፊዎችና ሰራተኞች የሚሰጡ አገልግሎቶችን ጥራትና ቅልጥፍና በማሻሻል የተገልጋዩን ማህብረሰብ እርካታ ለማሳደግ በተነሳሽነት ተግተው ሊሰሩ እንደሚገባ ተገልጻል፡፡