በእሳትና በድንገተኛ አደጋዎች ላይ የህብረተሰቡን ግንዛቤ በማስፋት አደጋዎችን ቀድሞ ሳይደርሱ መከላከል እንደሚገባ ተገለጸ፡፡

user 03-Jun-2025 ልማት

በእሳትና በድንገተኛ አደጋዎች ላይ የህብረተሰቡን ግንዛቤ በማስፋት አደጋዎችን ቀድሞ ሳይደርሱ መከላከል እንደሚገባ ተገለጸ፡፡

‎የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ከእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ጉለሌ ቅርጫፍ ጽ/ቤት ጋር በጋራ በመሆን ከ10ሩም ወረዳ ለተወጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በ2017 በአደጋ ትግበራ ዙሪያ የፓናል ውይይት አካሄዷል ፡፡

‎በፓናል ውይይቱ ማስጀመሪያ ላይ ተገኝተው መልዕክታቸውን ያስተላለፉት የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ ወገሴ እንደተናገሩት ክፍለ ከተማው ከአደጋ ስጋት ነጻ የሆነ እዲሆንና ለነዋሪዎች ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር በርካታ ተግባራት እየተከናወነ ይገኛል ህብረተሰቡን ለአደጋ ተጋላጭነትን የተለዩ ችግሮችን አብዛኛውን በመፍታት አበረታች ሰራዎች መከናወናቸውን አንስተው የህብረተሰብን የአደጋ ሰራ ግንዛቤ በማሳደግ አደጋዎችን ቀድሞ ከመድረሳቸው በፊት ቀድሞ በመከላከል ትኩረት ሰጥቶ መስራተ እደሚገባ ተናግረዋል ፡፡

Related Post

ልዩ ዜና