በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር 1ኛ ዙር የገጽ ለገጽ የእንጠያየቅ መድረክ ተካሄደ።

user 06-Nov-2025 ልማት

በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር 1ኛ ዙር የገጽ ለገጽ የእንጠያየቅ መድረክ ተካሄደ።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ጽ/ቤት ፣ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤትና ከክፍለ ከተማው መልካም አስተዳደር አቤቱታ ቅሬታ አስተዳደር ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት የ1ኛ ዙር ‹‹ የእንጠያየቅ መድረክ ›› አካሄደ::

‎በመድረኩ ላይ የተገኙት ‎የጉለሌ ክፍለ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ድሪባ ታደሰ እንደተናገሩት በባለፉት ዙሮች በተካሄደው የእንጠያየቅ መድረክ ከህብረተሰቡ የተነሱ ጥያቄዎች የመፍታት ስራዎች ተሰርቷል በዚህም የህብረተሰቡን የአገልግሎት ፍላጎት ለማርካት በተለያዩ ጊዜ ድጋፍና ክትትሎችን በማድረግ፣ የህብረተሰቡን የአገልግሎት እርካታን ያለበትን ደረጃ ጥናት በመስራት እንዲሁም ሪፎርም የተደረጉ ተቋማት ለአገልግሎት ጥራት ቅድሚያ እንዲሰጡ የተደረገበት የአንድ ማእከል አገልግሎት በትኩረት እተሰራበት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሰርካለም ተፈሪ በበኩላቸው በክፍለ ከተማው አገልግሎት አሰጣጥ ስርዓቱን ለማዘመንና የተገልጋይን እርካታ ለማረጋገጥ በትኩረት የተሰራበት እንደሆነ ገልጸው የእንጠያየቅ መድረኩ የህብረተሰቡን ጥያቄ ፊት ለፊት ከሃላፊው ጋር በመገናኘት እየመለስን እንገኛለን ብለዋል፡፡

‎ህብረተሰቡ የሚፈልገውን አገልግሎት በጥራትና በፍጥነት ተደራሽ የማድረግና ብልሹ አሰራሮችን የመዋጋት መንግስት ለሕዝቡ የገባው ቃል በመሆኑ ይህን ተግባር የክፍለ ከተማው አስተዳደር እንደ ቁልፍ አጀንዳ ይዞ እየሰራበት ይገኛል ብለዋል፡፡

‎በመድረኩ ላይ የክፍለ ከተማው ሴክተር መስሪያ ቤቶች ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ፣ ጤና ጽ/ቤት ፣ ንግድ ጽ/ቤት ፣ መንግስት ቤቶች አስተዳደር ፣ መስሪያ ቦታዎች ልማትና ፣ የመሬት ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤትና የ መልካም አስተዳደር ቅሬታና አቤቱታ ጽ/ቤት አቅርበዋል፡፡

Related Post

ልዩ ዜና