በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በ2018 በጀት ዓመት በርካታ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶች እየተከናወኑ ይገኛል።
አስተዳደሩ በልዩ ትኩረት የትምህርት ዘርፉ ጥራትና ተደራሽነት ለማሳደግ ፣ የጤና ተቋማት ግንባታ ሂደት ፣ የወጣቶችና የሴቶችን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ መስሪያ ቦታዎች በልዩ ትኩረት በማከናወን ላይ ነው።
ከነዚህም መካከል አንዱ በጉለሌ ክፍለ ከተማ የሚገኘው በጉድሰመሪታ ሳይት የሚገኘው G+4 የመስሪያ ቦታ ግንባታ ሲሆን በአጭር ጊዜ ተጠናቆ ለተጠቃሚዎች ባሳለፍነው ቀናት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል።
በዚህም ለበርካታ ሴቶችና ወጣቶች በተለያዩ ዘርፎች የስራ ዕድል ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል