ጠንካራ የሲቪል ማህበራት ለጠንካራ ሀገረ መንግስት ግንባታ!
በጉለሌ ክፍለ ከተማ ከሁሉም ወረዳዎች የተውጣጡ የሲቪል ማህበራት ''ጠንካራ የሲቪል ማህበራት ለጠንካራ ሀገረ መንግስት ግንባታ'' በሚል መሪ ቃል የማጠቃለያ መድረክ ውይይት ተካሄደ።
በሀገራዊ አንድነት ላይ በህብረት መቆምና አብሮነትን በማሳደግ ሀገረ መንግስት ለመገንባት ትውልድ ላይ ተከታታይነት ያለው ሥራ ለመሰራት፣ ከነጠላ ትርክት ይልቅ የወል ገዥ ትርክት ብሔራዊነትን በጋራ በመገንባት ጠንካራ ማህበራት ለጠንካራ መንግስት ያለው ሚና ከፍተኛ መሆኑን በመገንዘብ በቅንጅት እና በትብብር ኃላፊነትታቸው መወጣት በሚችሉበት ዙርያ ውይይት ተደርጓል።
በመድረኩ ተገኝተው መልእክት ያስተላለፉት በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የዲሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ሃላፊ አቶ የኋላሸት በቀለ በባለፉት ለዉጥ ዓመታት በሀገራችንና በከተማችን የተመዘገቡ ፖለቲካዊ፤ ኢኮኖሚያዊ፤ ማህበራዊና ዉጭ ግንኙነት ዘርፎች የነበሩ ስኬቶችና ተግዳሮቶችን ላይ ቀጣይነት ሚናቸውን መወጣት እንዲችሉና የሀገራችንን የዕድገት ሂደቱን ይበልጥ ለማፋጠን የዳበር ዲሞክራሲ በመገንባት በመደመር መርህ አካታች የሆነ ሁሉ አቀፍ ለዉጥና ዕድገት በማምጣት የልማት፤ መልካም አስተዳደርና በዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ከከተማ አስተዳደሩ ጎን በመሆን የአባሎቻቸው ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ እንደሚገባ ገልጸዋል።
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ወልዴ ወገሴ መንግስት መሰረተ ልማትንና መሰል አገልግሎቶችን በማቅረብ ልማትና መልካም አስተዳደር ዕውን ለማድረግ አገልግሎት በዘመናዊ ቴክኖሎጅ የተደገፍ እንዲሆን በርካታ ውጤቶች እየተመዘገቡ ይገኛል። ይህም ተጠናክሮ እንዲቀጥል በየደረጃ ባሉ መዋቅሮች ዉስጥ የሚገኙ የሲቪል ማህበራት አደረጃጀቶች አስተዳደሩ በሚያከናዉናቸው ልማትና መልካም አስተዳደር ሥራዎች ዉጤታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን ሚና በመወጣት ሁሉም ዜጎች የሚጠበቅባቸው ኃላፊነት በብቃትና በታማኝነት ሀላፊነታቸውን መወጣት እንደሚገባ ገልጸዋል።