በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 አስተዳደር በ2018 ዓ.ም የክረምት በጎ ፈቃድ አካል የአቅመ ደካማ ቤት እድሳት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሄደ።

user 10-Jul-2026 ፖለቲካ

በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት "በጎነት በተግባር" በሚል መሪ ቃል በወጣቶችና ስፖርት በኮሙኒኬሽ እና ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤቶች አስተባባሪነት የ2018 በጀት ዓመት የክረምት በጎ ፈቃድ መርሃ-ግብር አካል የሆነውን የአቅመ ደካማ ወገኖች የመኖሪያ ቤት እድሳት ስራ በይፋ ተጀምሯል።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ይከበር ስማቸው በመርሃ-ግብሩ ማስጀመሪያ ላይ ባደረጉት ንግግር ለአቅመ ደካሞች መቆም ማለት ለህሊና መኖር ማለት እንደሆነና ጉልበት በደከመበት ፣አቅም ባነሰበት ጊዜ የወገኖቻችንን የቤት ችግር ለመቅረፍ እጃችንን መዘርጋታችን ትልቅ በረከት ነው ሲሉ የገለፁ ሲሆን ማህበራዊ ትስስርና አብሮነት ያጠናከረ እና የመተጋገዝ ባህላችንን ያሳደገ ተግባር በመሆኑ የበርካታ አቅመ ደካሞች ጎጆ በማቃናት ሸክማቸውን ማቃለል ይገባናል ብለዋል።

በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 4 አስተዳደር የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ትዕግስት ተሾመ በበኩላቸዉ የ2018 በጀት አመት የክረምት በጎፈቃድ መርሀ ግብር የሆነውን የአቅመ ደካማ ወገኖች የመኖሪያ ቤት እድሳት ስራ በወረዳው በተለምዶ ጉቶ ሜዳ ተብሎ የሚጠራው ሰፈር ያስጀመርነዉ ተግባር ከራስ አልፎ ለሌላው ደስታ መትረፍ መሆኑን ገልፀዉ በተለይም አቅመ ደካማ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን መደገፍና ከጎናቸው መቆም የሁላችንም የዜግነት ግዴታ እንደሆነና ከዛሬ ጀምሮ ሁሉም ተቋም የበጎ ፍቃድ ስራዉን በሁሉም ተግባራት ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

በመርሀ ግብሩ ላይም ጥሪ የተደረገላቸዉ የክ/ከተማ እና የወረዳ አመራሮች ወጣቶችና የአካባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

Related Post

ልዩ ዜና