በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የተቀናጀ 4ኛ ዙር የፖሊዮ በሽታ መከላከያ ክትባት ዘመቻ በይፋ ተጀመረ!

user 13-Dec-2025 ማህበራዊ ጉዳዮች

በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የተቀናጀ 4ኛ ዙር የፖሊዮ በሽታ መከላከያ ክትባት ዘመቻ በይፋ ተጀመረ!

በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ሸጎሌ ጤና ጣቢያ አሰባባሪነት ከትምህርት ጽ/ቤት ጋር በመሆን በምዕራፍ ቅድመ አንደኛ እና መካከለኛ ት/ቤት የተቀናጀ የፖሊዮ በሽታ መከላከያ ክትባት አስጀምረዋል።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሄለን አሰፋ እንደገለፁት ከዛሬ ታህሳስ 3 ጀምሮ እስከ ታህሳስ 6/2108ዓ.ም በዘመቻ መልክ የሚሰጠውን የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት እድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ ህጻናትን በሙሉ ወላጆችና አሳዳጊዎች እንዲያስከትቡ በመጥቀስ ክትባቱ በጠናከረ መልኩ እንዲቀጥል አስፈላጊውን የቅርብ ድጋፍና ክትትል እየተደረገ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 የብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አበባው አለምነህ በበኩላቸው እየተሰጠ የሚገኘው 4ኛ ዙር የፖሊዮ በሽታ መከላከያ ክትባት ወላጆች ለስኬታማነቱ በተጠቀሱት ቀናት ልጆቻቸውን እንዲያስከትቡ አሳስበዋል።

የሸጎሌ ጤና ጣቢያ ሜዲክል ዳይሬክተር አቶ ለሜሳ ኃይሉ ክትባቱ በትምህርት ቤቶች፣ቤት ለቤትና በህጻናት መዋያ ላይ በባለሙያዎች አማካኝነት በጠብታ መልክ እንደሚሰጥ ገልጸው ይሄን ተግባራዊ እንዲሆን እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

Related Post

ልዩ ዜና