በጎ ፈቃደኝነት ለማህበረሰብ ለውጥ !!

user 07-Aug-2025 ማህበራዊ ጉዳዮች

በጎ ፈቃደኝነት ለማህበረሰብ ለውጥ !!

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የ2017 ዓ.ም የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ‹‹ የህይወት ልምዴን ለወጣቱ ›› ከ10ሩም ወረዳ ለተወጣጡ ወጣቶች አካሄዷል፡፡

(ጉለሌ ኮሙኒኬሽን ፣ 30-11-2017 ዓ.ም)

በስነ ስርዓቱ ላይ ‹‹ የህይወት ልምዴን ለወጣቱ ›› በሚል የጌርጌሴኖን አዕምሮ ህሙማን መርጃ ማህበር መስራችና ዋና ስራ አስኪያጅ ሊቀ ትጉሃን መለሰ አየለ ፣ የግጥምና ዜማ ደራሲ አቶ ሙሉ ገበየሁ ያለው የህይወት ልምዳቸውንና ተሞክሯቸውን ለወጣቶች አጋርቷል የዕለቱም ልዩ ተሸላሚ ሆነዋል፡፡

በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ ወገሴ የአሁኑ ትውልድ ካለው ጊዜና ገንዘብ ቀንሶ ለበጎ ተግባራት በማዋል አረጋውያንና አቅመ ደካማ ቤተሰቦችን በመደገፍና በመንከባከብ የዜግነት ማህበራዊ ኃላፊነታችንን በመወጣት አሻራችንን ማኖር ይገባናል። በዚህ ክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ፕሮግራም ሁሉም ማህብረሰብ በሰው ተኮር ተግባራትን የነቃ ተሳትፎ ከማድረግ ባለፈ ክፍለ ከተማችንን የመደጋገፍና የአብሮነት እሴት በማጠናከር የተቸገሩ ወገኖችን ደስታ መጋራት አለብን ብለዋል፡፡

Related Post

ልዩ ዜና