የጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በመጪው ቀናት በሚከበሩ የመስቀል ደመራና የኢሬቻ በዓላት ፍጹም ሰላማዊ ሆኖ እንዲከበር በትኩረት እየሰራ መሆኑ ተገለጸ።

user 20-Sep-2025 ወቅታዊ ጉዳይ

የጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በመጪው ቀናት በሚከበሩ የመስቀል ደመራና የኢሬቻ በዓላት ፍጹም ሰላማዊ ሆኖ እንዲከበር በትኩረት እየሰራ መሆኑ ተገለጸ።

(ጉለሌ ኮሙኒኬሽን ፣ 10 -01 -2018 ዓ.ም)

በአስተዳደሩ በመጪው ቀናት በሚከበሩ የመስቀል ደመራና የኢሬቻ በዓላት ፍጹም ሰላማዊ ሆኖ እንዲከበር እየተከናወኑ ያሉትን የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን የከተማ ደጋፊ አመራሮች ከክፍለ ከተማና ከወረዳ አመራሮች ጋር ገምግሟል።

በውይይቱ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ፣ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ እንደተናገሩት በመጪዎቹ ቀናት የምናከብራቸው በዓላት ባህላዊ መገለጫዎችንና የጋራ እሴቶቻችንን ከማጎልበት ባለፈ አንድነታችንን ለማጠናከርና ለአገር ግንባታ ወሳኝ ናቸው።

ዛሬም እንደትናንቱ የጋራ መስተጋብራችን ደምቀዉ የሚታዩበት የመስቀል ደመራና የኢሬቻ በዓል ፍፀም ሰላማዊ ሆኖ እንዲከበር ከሁሉም ነዋሪዎች ጋር የጋራ መግባባት መፍጠርና ይህንንም መላው መዋቅራችንና አመራሩ የድርሻውን በአግባቡ መወጣት ይኖርበታል ብለዋል፡፡

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ ወገሴ በበኩላቸው አመራሩ እያከናወናቸው ያሉትን ተግባር አጠናክሮ በማስቀጠል በዓላቶቹ ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዳይከበር የሚሰሩ ኃይሎችን ቀድሞ መለየትና ማክሸፍ ተቀዳሚ ተግባር መሆን እንደሚገባ ገልጸዋል። የከተማችንን ብሎም የክፍለ ከተማችንን ደህንነት በማረጋገጥ፣ ሕብረ ብሔራዊ አንደነታችንን የማጠናከር ሥራን ማጎልበት ይኖርብናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የክፍለ ከተማው ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ምክትልና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ገነት ዋቅጋሪ በበኩላቸው ከፊታችን የምናከብራቸው በአደባባይ በዓላት ሰላማዊ ሆነው እንዲከበሩ በትኩረት መስራት አለብን ለዚህም የክ/ከተማችን ነዋሪዎችን የሰላሙ ባለቤት ማድረግ ይጠበቅብናል።

የመስቀል ደመራና ኢሬቻን በዓላት በዓደባባይ የሚከበሩ በመሆናቸው ይህንን እንደ ምቹ አጋጣሚ ተጠቅመው የተጀመረዉን የብልጽግና ጉዞ ወደ ኃላ ለመመለስ እየጣሩ ያሉ ኃይሎችን እየታገልን ሁሉም በዓላት በሰላም እንዲከበሩ መስራት ይኖርብናል ብለዋል።

Related Post

ልዩ ዜና