የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የልማት ፕሮጀክት ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል ከሁሉም ዜጋ የሚጠበቅ ተግባር መሆኑን ነዋሪዎች ገለጹ

user 28-May-2026 ልማት

የቀበና የወንዝ ዳርቻ የልማት ፕሮጀክት ለማህበረሰቡ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ መሆኑን ነዋሪዎቹ ገልጸዋል

ከዚህ በፊት ከተለያዩ ቦታዎች የቆሸሸ ውሀና የሽንት ቤት ፍሳሽ በቀበና ወንዝ በመልቀቅ ለብዙ ዘመናት የመልካም አስተዳደር ጥያቄና ለነዋሪዎች የጤና ችግር እየፈጠረ የነበረበትን ሁኔታ በማውሳት በአሁኑ ስአት እንደ ሀገር የቱሪዝም መስህብ በማድረግና ለወጣቱ የስራ ዕድል ፈጠራና ለነዋሪው ምቹ አካባቢን በመፍጠር የማህበረሰቡ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ያረጋገጠ መሆኑን ወጣት ቢኒያም ሀሳቡን ተናግሯል ።

በተጨማሪም ወጣት ናትናኤል አበበ እንዳነጋገርነው ሀገራዊ ልማትን በማፋጠን የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች የተከናወኑ ተግባራትን በማስቀጠልና ለትውልድ በማስተላለፍ አማራጭ የማይሰጠው የወጣቱ እጣ ሲሆን የቀበና የወንዝ ዳርቻ የልማት ፕሮጀክት በውስጡ የያዛቸው የአገልግሎት ሰጭ ዘርፎች ለበርካታ ወጣት የስራ እድል የፈጠረና ተጠቃሚ መሆኑን አስተያየቱን ሰጥቷል።

በተጨማሪም የአዲስ አበባ ከተማ የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት ተግባራት ኢትዩጵያ ለሌሎች ሀገራት የመሰከሩላት የአፍሪካ ተምሳሌት መሆኗን የተረጋገጠበትና አንዱ የለውጥ ማሳያ የሆነውን ተግባር በማጠናከር ከሁሉም ዜጋ የሚጠበቅ ተግባር መሆኑን ሀሳቡን ገልጿል።

Related Post

ልዩ ዜና