በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የ2017 ዓ.ም የቡሄ በዓል በድምቀት ተከበረ::
በክፍለ ከተማው ባህል፣ ኪነጥበብና ቱሪዝም ጽ/ቤት አዘጋጅነት በተካሄደው የቡሄ በዓል አከባበር ላይ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ተከብሮ ውሏል፡፡
በበዓሉ አከባበር ላይ የተገኙት አቶ ወልዴ ወገሴእንደተናገሩት የቡሄ በዓል የኢትዮጵያውያን ልዩ ከሆኑት እሴቶች አንዱ ነው ያሉ ሲኋን ባህላዊ ትውፊታዊ የሆኑ ሃብቶቻችንን በመጠበቅ ለመጭው ትውልድ ማስተላለፍ የኢትዮጵያዊያን መለያ የሆኑ እሴቶችን በማሳደግ መጤና ጎጂ ባህሎችን ማስወገድ ይገባናል ፡፡
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ባህል፣ ኪነጥበብና ቱሪዝም ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ አባይነሽ ቴኒ በበኩላቸው ቡሄ ሲመጣ የክረምቱ ጨለማነት አልፎ ወደ ብርሃን ወደ ጥቢ የሚያመራበት፣ ወገግታ የሚታይበት ፤ ሰማይ ከጭጋጋማነት ወደ ብሩህነት የሚሸጋገርበት ወቅት በመሆኑ ከቡሄ በጏላ መሆኑን ትውፊቱ ያስረዳል ብለዋል፡፡