የጉለሌ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ከተጠሪ ተቋማቱ ከክፍለ ከተማው ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ፣ ከክፍለ ከተማ ሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት ፣ ከእሳትና ድንገተኛ አደጋ ስራ አመራር ጉለሌ ቅርንጫፍ ጋር በጋራ በመሆን የ2018 ዓ.ም የ8ኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሄዷል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አንዓለም ክብረት እንደተናገሩት የአረንጓዴ አሻራ ባለፉት ዓመታት በተክልናቸው ችግኞች የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ የአየር ንብረት ጫናን ለመከላከል አስተዋፅኦ አበርክቷል በመሆኑም የአረንጓዴ አሻራ ተግባራችንን በማጠናከር የጀመርነውን ልማትና ብልጽግና እናረጋግጣለን ብለዋል።
የክፍለ ከተማው ሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሚሊዮን ቱራ በክፍለ ከተማው የነዋሪዎች ወሳኝ ኩነት መረጃዎችን ተደራሽ ከማድረግ ባሻገር በዛሬው ዕለትም ሀገራዊ አጀንዳችን የሆነው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የዚህ ማሳያ እንደሆነ ገልጸዋል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች ፣ የጽዳት አምባሳደርና ባለሙያዎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ፣የአካባቢው ነዋሪዎች ተሳትፈውበታል።