የፀጥታ አካላት ከህዝባዊ ሰላም ሰራዊት ጋር በቅንጅት በመስራት የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት ማስጠበቅ እንደሚገባ ተገለጸ።

user 29-May-2026 ፖለቲካ

የፀጥታ አካላት ከህዝባዊ ሰላም ሰራዊት ጋር በቅንጅት በመስራት የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት ማስጠበቅ እንደሚገባ ተገለጸ።

በጉለሌ ክፍለ ከተማ ጥምር የፀጥታ አካላት ፣ ህዝባዊ የሰላም ስራዊት እና የሸገር ሲቲ ኢጀርሳ ጎሮ የፀጥታ አካላት በአንድ ማዕከል የፀጥታ ስምሪት ተሰጠ::

በክፍለ ከተማው የጥምር ጸጥታ አካላት እና የሰላም ሰራዊት የተቀናጀ የአንድ ማዕከል ስምሪት በዋናነት የህዝቡን ደህንነት በንቃት ለመጠበቅና ነዋሪው ያለምንም የጸጥታ ስጋት እንዲንቀሳቀስ ለማስቻል የተዘጋጀ ነው።

በአንድ ማዕከል የስምሪት መርሃ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ እንደተናገሩት ሰላም የሁሉንም ትብብር የሚፈልግ ዋነኛ ጉዳይ መሆኑን ህዝባዊ የሰላም ሰራዊት አባላት አካባቢያቸውን በመጠበቅ በተግባር ውጤታማ የፀጥታ ስራ እየሰሩ እንደሆነ ገልጸው ይኸንንም አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል ።

ጥምር የጸጥታ አካላትና የሰላም ሰራዊቱ የተጣለባችሁን ህዝባዊ አደራ በመገንዘብ በቀንም ሆነ በሌሊት በከፍተኛ ንቃት የከተማዋን ሰላም ለማስጠበቅ ዝግጁነትን ማጠናከር እንደሚገባ ተናግረዋል።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ ወገሴ በበኩላቸው የአንድ ማዕከል ጥምር የጸጥታ አካላት ስምሪት በክፍለ ከተማው ያለውን የጸጥታ መዋቅር ይበልጥ በማጠናከር የአካባቢያችንን ሰላም ሊያደፈረሱ የሚችሉ አካላትን በነቂስ መከታተልና ፀጉረ ልውጥ አካላት ወቅቱን በመጠቀም የተለያዩ የፀጥታ ችግሮች እንዳይፈጥሩ ማህበረሰቡ ላይ የሰላም ሰራዊቱ ህዝባዊ ኃላፊነቱን በመወጣት ከመንግሥትና ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት መንቀሳቀስ ከመቼውም ጊዜ በላይ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት መልክታቸውን አስተላልፈዋል ።

Related Post

ልዩ ዜና