የኮሙኒኬሽን ዘርፉ ሙያዊ ስነ-ምግባርን ተላብሶ ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃዎችን በጥራት በመስራት ተደራሽ ማድረግ እንዳለበት ተገለጸ።
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወራት ዕቅድ አፈጻጸሙንና የቀጣይ 6 ወራት የተከለሰ ዕቅዱን ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አድርጓል።
ጽ/ቤቱ በባለፉት 6 ወራት ተቋሙ የመንግስት ስራዎች በተገቢው መንገድ እንዲደርስ የተሰራበት ፣ የህብረተሰቡን የአገልግሎት አሰጣጥና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፍትሔ እንዲያገኙ ሚናውን በመወጣት የክፍለ ከተማ አስተዳደሩን ስራዎችን ለህብረተሰቡ ትክክለኛ መረጃ እንዲያገኝ ትኩረት ሰጥቶ የተሰራበት እንደነበር ተብራርቷል ።
በበጀት አመቱ በባለፉት 6 ወራት በማህበራዊ ፣ በኢኮኖሚያዊና በወቅታዊ ጉዳዮች በተመለከተ ዜናዎችን፣አጫጭር ፕሮግራሞችን ፣የተለያዩ የህትመት ውጤቶችን እና የህዝብ ፓናል ውይይቶችን በወቅቱና በጥራት በማዘጋጀት ባሉት የኮሙኒኬሽን አግባቦች በመጠቀም በተለያዩ በማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች በስፋት ማሰራጨት መቻሉን በቀረበው ሪፖርት ተገልጿል፡፡
መድረኩን የመሩት የጉለሌ ክፍለ ከተማ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሰርካለም ተፈሪ እንደተናገሩ በበጀት ዓመቱ በባለፉት 6 ወራት በርካታ የኮሙኒኬሽንና የህዝብ ግንኙነት ስራዎች የተሰሩበት መሆኑን ገልፀው፣ መንግስት የሚሰጠውን አገልግሎትና በህዝቡ የሚነሱ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ መረጃ በመስጠት እንዲሁም፣ የክፍለ ከተማው መልካም ገጽታ በማጉላት በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ገልጸዋል።