የጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በ90 ቀናት ዕቅዱ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመመለስ እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራትን ገምግሟል።
(ጉለሌ ኮሙኒኬሽን ፣ 16 -10 -2017 ዓ.ም)
አስተዳደሩ በ90 ቀናት ዕቅዱ በ10 ቀናት አፈጻጸሙ የማህበረሰቡን ቁልፍ ችግሮች ሊፈቱ የሚችሉ የወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠራ ፣ የከተማ ግብርና የሌማት ትሩፋት ስራዎችን ፣ የአረንጓዴ አሻራ ተግባር ፣ የኑሮ ውድነትን ማረጋጋት ፣ የክረምት በጎ ፈቃድ ተግባራት ፣ የትምህርት ዘርፎች ስራዎች ፣የኮሪደር ስራዎች ማጠናቀቅ ፣ በክፍለ ከተማው እየተሰሩ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን ማጠናቀቅ ፣ የሰላም ግንባታ ፣የገቢ አሰባሰብ ፣ ልመና ተረጂነት ማስወገድ ፣ የመልካም አስተዳደር አገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻል ፣ የፋይዳ መታወቂያ ምዝገባ ንቅናቄ ፣ የኮሙኒኬሽንና ህዝብ ዙሪያ ግንኙነት ስራዎችን ማጠናከር ላይ የተከናወኑ ተግባራትን ከክፍለ ከተማና ከወረዳ አመራሮች ጋር ገምግሟል ።
በመድረኩ ላይ የተገኙት ምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ጀማሉ ጀምበር እንደተናገሩት አመራሩ የማህበረሰባችንን ሁለንተናዊ ችግር ለመፍታት ቁርጠኛ በመሆን ልምድና ሌሎች ተሞክሮዎችን በመቀመር በእቅዱ የተመላከቱ ተግባራትን ከህብረተሰቡ ጋር በመተባበር የሚከናወኑ ተግባራት ጥራታቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ በየደረጃው ያለው አመራር የቅርብ ክትትል በማድረግ ፣ ቅንጅታዊ አሰራሮችን መጨመር ፣ የድጋፍና ክትትል አግባብ ሂደትን ማሻሻል በቀጣይ በትኩረት መሰራት እንዳለበት አቅጣጫ አስቀምጠዋል ።
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ ወገሴ በበኩላቸው በክፍለ ከተማችን እየተከናወነ የሚገኘው የ90 ቀናት ዕቅድ ተግባሮቻችን በክፍለ ከተማችን ዕውን እንዲሆን አመራሩ ለሚከናወነው ተግባራት ወቅቱን የሚጠበቀውን ፍጥነትና ውጤት በማምጣት በጊዜ የለኝም መንፈስ ቆጥሮ በመስጠትና በመቀበል ውጤታማ ተግባራትን ማከናወን አለብን ብለዋል።
የክፍለ ከተማው ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ይከበር ስማቸው በበኩላቸው በክፍለ ከተማው በ90 ቀናት የሚተገበሩት ተግባራትን ለቅሞ በመፈጸም የህዝባችንን የመልካም አስተዳደርና የልማት ጥያቄዎች የምንመልስበት በመሆናቸው አመራሩ ተገቢውን ትኩረት ሰጥቶ መስራት ይገባል ብለዋል።