የጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በመደበኛነትና በንቅናቄ እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራትን የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች በተገኙበት ገምግሟል።
አስተዳደሩ 2ኛ ዙር የ3 ወራት የሴቶችና የወጣቶች ስራ ዕድል ፈጠራ ፣ የከተማ ግብርና የሌማት ትሩፋት ተግባራት እንዲሁም መደበኛ ተግባራትን ከክፍለ ከተማና ከወረዳ አመራሮች ጋር በመገምገም አቅጣጫ ተሰጥቶበታል።
መድረኩን የመሩት የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ ወገሴ እንደተናገሩት አመራሩ ከግምገማ ስርዓት ተላቆ በወቅቱ ተልዕኮ ተቀብሎ የማስፈጸም አቅሙን ሊያሳድግ ይገባል ያሉ ሲሆን የሚሰጡ ተግባራት ቆጥሮ በእኩል ማስኬድ ያስፈልጋል የሚመጡ ተልዕኮች የህብረተሰቡን የመልካም አስተዳደርና የልማት ጥያቄዎችን የሚፈቱ በመሆኑ ሁሉንም በእኩል በማስኬድ ውጤት ማምጣት ያስፈልጋል በመሆኑም የስራ ዕድል ፈጠራ ፣ የከተማ ግብርናና የሌማት ትሩፋት ፣ የኑሮ ማረጋጋትን አስተዳደሩ በጥብቅ ዲስፕሊን የሚመራቸው ተግባራት መሆናቸውን ገልጸዋል።
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ይከበር ስማቸው በበኩላቸው የወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠራና የከተማ ግብርና ስራዎቻችን ዋነኛ የፓርቲያችን ትኩረት በመሆኑ አመራሩ የስምሪት ስራዎችን በቁርጠኝነት የሚመራና የሚያስቀጥል ሊሆን እንደሚገባ ፣ የፓርቲና የመንግስት ስራዎችን አቀናጅቶ መምራት፣ ተቋም መገንባት፣ የህዝብ አንገብጋቢ ችግር መፍታትና ማህበረሰቡን ማሳተፍ ፣ ተገቢውን አገልግሎት መስጠት ፣ የፓርቲውን መርህና እሴት ወደ ህዝብ ማስረፅ ፣ የመረጃ ጥራትና ተደራሽነትን ማረጋገጥ እንደሚገባ አሳስበዋል።
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚና ስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰለሞን ታደሰ በበኩላቸው ሁሉም አመራር የሚመጡ ተልዕኮችን የማስፈጸም አቅሙን በመጨመርና ስራዎችን አስተሳስሮ መምራት ያስፈልጋል በክፍለ ከተማው የሚከናወኑ ሁሉም ተግባራት የህብረተሰባችንን ተጠቃሚነት በተግባር የሚያረጋግጥ በመሆኑ በተሰጠን ጊዜ ውስጥ ማሳካት አለብን ብለዋል።