የመስቀል እና የኢሬቻ በዓላት ሃይማኖታዊና ባህላዊ ትውፊታቸውን በጠበቀ መልኩ በሰላም እንዲከበር ሴቶች የበኩላቸውን አስተዋጽዖ መወጣት እንደሚገባቸው ተገለፀ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶችና ህፃናት ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ "በእምርታና በማንሰራራት የታጀበ በዓላትን እናክብር "በሚል መሪ ቃል በመጪው ለቀናት የሚከበሩ የመስቀልና የኢሬቻ በዓላት አከባበር ዙሪያ ከ11ክፍለ ከተማ ከተወጣጡ ሴቶች ጋር ውይይት ተደረገ።
በመድረኩ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች ፣ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ እንደተናገሩት የመስቀል ደመራ በዓለም ቅርስነት የተመዘገበ እንዲሁም የኢሬቻ በዓል የኢትዮጵያዊነታችን አንዱ መገለጫ በመሆኑ የኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን የዓለም በዓል ጭምር ስለሆነ ሃይማኖታዊና ባህላዊ ትውፊታቸውን በጠበቀ መልኩ በሰላም እንዲከበሩ ህብረተሰቡ ሃላፊነቱን መወጣት አለበት ሲሉ ተናግረዋል።
በዓላቶቹ በሰላምና በድምቀት እንዲከበሩ ሴቶች ዋነኛ ባለቤቶች በመሆናቸውን የገለፁት ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ አያይዘው የመስቀልና የኢሬቻ ስናከብር የራሳቸውን እሴቶችና ቱዉፊቶች ሳይለቁ እንዲከበሩ የራሳችንን አስተዋጽኦ ማበርከት ይገባል በማለት ገልፀዋል።