የጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የ2017 በጀት ዓመት የመንግስትና የፓርቲ ስራዎች አፈጻጸምን ከአጠቃላይ አመራር ጋር የግምገማ መድረክ ተካሄደ።

user 19-Jul-2025 ወቅታዊ ጉዳይ

የጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የ2017 በጀት ዓመት የመንግስትና የፓርቲ ስራዎች አፈጻጸምን ከአጠቃላይ አመራር ጋር የግምገማ መድረክ ተካሄደ።

አስተዳደሩ በበጀት ዓመቱ ሁሉንም አቅሞች አቀናጅቶ በመጠቀም በክፍለ ከተማው በማህበራዊ ፣በኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ እንዲሁም በሰላምና ፀጥታ ዘርፎች በርካታ ስኬቶችን ማስመዝገብ መቻሉን በሪፖርቱ የተገለጸ ሲሆን።

የዋጋ ግሽበት ለመከላከል የዋጋ ንረት በሚፈጥሩ ነጋዴዎች ላይ ቁጥጥር የማድረግ፣በሸማች ማህበራት እና በእሁድ ገበያዎች የፍጆታ እቃዎችን ለነዋሪዎች በተመጣጣኝ ዋጋ ተደራሽ የማድረግ ፣ የአገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል በአንድ ማዕከል ተጠናክሮ መቀጠሉ ፣የክፍለ ከተማውን ሰላምና ፀጥታ ለማስጠበቅ የሰላም ሰራዊቱን የማደራጀት የማብቃትና አካባቢያቸውን እንዲጠብቁ የማድረግ ፣የስጋት ቦታወችን በመለየት የመስራት እንዲሁም ከአጎራባች ክፍለ ከተሞች እና የኦሮሚያ ከተሞች ጋር ተቀናጅቶ በመሰራት ወሰን ተሻጋሪ ወንጀሎችን የመቀነስና በጋራ የመከላከል ስራ ውጤት የተመዘገበባቸው ተግባራት መሆናቸው ተገልጿል።

Related Post

ልዩ ዜና