በመንግስት የሚሰጡ አገልግሎት ፍትሃዊና ቀልጣፋ እንዲሆን ለማስቻል የባለድርሻ አካላት ሚና የላቀ መሆኑ ተገለጸ።
(ጉለሌ ኮሙኒኬሽን ፣ 11 -11 -2017 ዓ.ም )
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ ቤት በመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ የተገልጋይና የባለድርሻ አካላት ሚና በሚል መሪ ቃል የውይይት መድረክ አካሂዷል።
በውይይት መድረኩ ላይ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ድሪባ ታደሰ እንደተናገሩት አብዛኛው አገልግሎቶች በመንግስት ተቋማት እንደሚሰጥ አንስተው ባለፉት አመታት የአገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመን እና ለተገልጋይ ምቹ ለማድረግ ሰፊ ስራዎች መሰራቱን ገልፀው የዛሬውም መድረክ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ከባለድርሻ አካላት በመስማት እና እንደ ግብአት በመውሰድ ለማረም ያለመ መሆኑን አስገንዝበዋል።