የጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በወቅታዊና በመደበኛ ተግባራት በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ በመደመር እይታ የዘርፎች እምርታ የኢንሼቲቭ ዋና ዋና ግቦች ዕቅድ ትግበራ ዙሪያ ከክፍለ ከተማና ከወረዳ አመራሮች ጋር ገምግሟል።

user 25-Feb-2026 ወቅታዊ ጉዳይ

የጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በወቅታዊና በመደበኛ ተግባራት በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ በመደመር እይታ የዘርፎች እምርታ የኢንሼቲቭ ዋና ዋና ግቦች ዕቅድ ትግበራ ዙሪያ ከክፍለ ከተማና ከወረዳ አመራሮች ጋር ገምግሟል።

አስተዳደሩ “በመደመር መንግሥት ዕይታ፣ የዘርፎች እመርታ” በሚል የተቀመጡ የኢኒሼቲቭ ስራዎችና የወጣቶችና ሴቶች ስራ ዕድል ፈጠራና የከተማ ግብርና የ90 ቀናት ዕቅድ የተግባራት አፈጻጸም ፣ የኑሮ ውድነት ማረጋጋት ፣ ተረጂነትን መቀነስ ፣ የምርጫ ምቹነት ያለበትን ደረጃ ከክፍለ ከተማና ከወረዳ አመራሮች ጋር ገምግሟል።

በመድረኩ ላይ የተገኙት የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ ወገሴ እንደተናገሩት በክፍለ ከተማው እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራት የህብረተሰባችንን ተጠቃሚነትን የምናረጋግጥበት በመሆኑ አመራሩ ስራዎች በተደራጀ አግባብ ለቅሞ በመያዝ የዕቅዱን ተፈጻሚነት ማረጋገጥ ያስፈልጋል ያሉ ሲሆን በወረዳዎች የምርጫ ምቹነት ማረጋገጥ ፣ የኢኔሺቲቭ ግቦችን የተደራጀ ዕቅድ በመገምገም የጋራ ተግባቦት በመያዝ ወደ ተግባር መግባት ያስፈልጋል ብለዋል።

የኢኒሼቲቭ ስራዎች ከመደበኛ ተግባራት ጋር ተቀናጅተው ሊከናወኑ ይገባል ያሉ ሲሆን በዕቅዱ ላይ የተመላከቱትን እያንዳንዱ ግቦች ማስፈጸሚያ ዕቅዶችን መሬት አውርዶ እንዲሳካ ማስቻል የልመናንና ተረጂነትን ዜሮ የማድረስ ግቦች በአግባቡ ማከናወን የስራ እድል ፈጠራን ማፋጠን እና ቀልጣፋ የአገልግሎት አሰጣጥን ማረጋገጥ እንደሚገባም ተናግረዋል።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰለሞን ታደሰ በበኩላቸው አስተዳደሩ በመደበኛ በወቅታዊነት ዕቅዶችን ይዞ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን በማከናወን ላይ ይገኛል በዚህም የወጣቶችና ሴቶች ስራ ፈላጊ የቴክኒካል ስልጠና በትኩረት ማከናወን ያሉ ሲሆን በቀጣይ ተረጂነትን መቀነስ ፣ የከተማ ግብርና የሌማት ትሩፋት ፣ የኑሮ ውድነትን ማረጋጋት ፣ የምርጫ ምቹነት ማረጋገጥ ስራዎች ፣ የኢኒሼቲቭ ተግባራትን በትኩረት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሽመልስ ጎዴቦ በበኩላቸው በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አሕመድ የተቀመጡ ግቦችና አቅጣጫዎች የህብረተሰባችንን ተጠቃሚነት የሚጨምሩ ዕቅዶቻችንን በእጥፍ ለማሳካት የሚረዳን ክፍለ ከተማችንን የለውጥ ተምሳሌት እንዲሆን የሚያስችል መሆኑን ገልጸው ከስራ እድል ፈጠራ ጋር የወጣቶች፣ሴቶች እና ነዋሪዎች ተጠቃሚ በማድረግ ፣ከሌማት ትሩፋት ነባር ተጠቃሚዎችን ምቀርት እንዲጨምሩ የተቀናጀ የከተማ ግብርና ስራዎች መስራት አዳዲስ ተጠቃሚዎችን ወደ ተግባር እንዲገቡ የጀመረውን ተግባር ይበልጥ በማጠናከር ሁሉም ስራዎችን በማቀናጀት በውጤት መተግበር ይገባል ብለዋል።

በመድረኩ ላይም በቀጣይ አፈጻጸሞች ላይ ልዩ ትኩረት የሚሹ አቅጣጫዎች እቅድ ቀርቦ ውይይት በማካሔድ የአፈጻጸም አቅጣጫ ተቀምጧል።

Related Post

ልዩ ዜና