የጉለሌ ክፍለ ከተማ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት " ዓላማ ተኮር ኮሙኒኬሽን " ዙሪያ በ10ሩም ወረዳ ለሚገኙ ለዘርፉ አመራሮች ፣ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጥቷል።
ስልጠናውን የሰጡት የጉለሌ ክፍለ ከተማ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አንተነህ ለታ እንደተናገሩት ስልጠናው የኮሙኒኬሽን ዘርፉ አመራሮችና ባለሙያዎች ዓላማ ተኮር የሆነ የኮሙኒኬሽን ስርዓትን በመዘርጋት ለህዝቡ ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ በማድረስ ለክፍለ ከተማችን ልማት እና አስተማማኝ ሰላም መስፈን በጋራ እንዲረባረብ ለማስቻል በእውቀት፣ በክህሎትና በተግባራዊ እንቅስቃሴው አቅሙን እያሳደገ መጓዝ እንደሚገባው ገልጸዋል።