የጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የ90 ቀናት ዕቅድ ውስጥ በ55 ቀናት የተከናወኑ የልማት ፣ የመልካም አስተዳደርና ሰው ተኮር ተግባራትን ገምግሟል።
(ጉለሌ ኮሙኒኬሽን ፣ 06 -12 -2017 ዓ.ም)
አስተዳደሩ በ90 ቀናት ዕቅዱ በባለፉት 55 ቀናት አፈጻጸሙ የማህበረሰቡን ቁልፍ ችግሮች ሊፈቱ የሚችሉ የወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠራ ፣ የከተማ ግብርና የሌማት ትሩፋት ስራዎችን ፣ የአረንጓዴ አሻራ ተግባር ፣ የኑሮ ውድነትን ማረጋጋት ፣ የክረምት በጎ ፈቃድ ተግባራት ፣ የትምህርት ዘርፎች ስራዎች ፣የኮሪደር ስራዎች ማጠናቀቅ ፣ በክፍለ ከተማው እየተሰሩ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን ማጠናቀቅ ፣ የሰላም ግንባታ ፣የገቢ አሰባሰብ ፣ ልመና ተረጂነት ማስወገድ ፣ የመልካም አስተዳደር አገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻል ፣ የፋይዳ መታወቂያ ምዝገባ ንቅናቄ ፣ የኮሙኒኬሽንና ህዝብ ዙሪያ ግንኙነት ስራዎችን ማጠናከር ላይ የተከናወኑ ተግባራትን እንዲሁም የጽዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ ዙሪያ ከክፍለ ከተማና ከወረዳ አመራሮች ጋር ገምግሟል ።
በመድረኩ ላይ የተገኙት የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ ወገሴ እንደተናገሩት በክፍለ ከተማችን በበጀት ዓመቱ የማይደፈሩ የነበሩና የማይነኩ የሚመስሉ መላው የክፍለ ከተማችን መዋቅርና ህብረተሰቡን በማስተባበር ታላላቅ ስራዎች ሰርተን ሌሎች ዕቅዶቻችን ኃይል የሚሆነን ስራ በመሆኑ አሁንም ለክፍለ ከተማችን ሁለንተናዊ ልማትና ሰላም መረጋገጥ በጋራ መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።
የክፍለ ከተማው ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ይከበር ስማቸው በበኩላቸው አመራሩ ከመቼውም ጊዜ በተለየ መልኩ ተግባርና ውጤትን መሰረት ያደረገ ግምገማዎችን በማድረግ ስኬታማ ውጤቶች ተመዝግበዋል ያሉ ሲሆን አሁንም ህብረተሰቡን በልማቶቻችን ውስጥ አጋር በማድረግ ያቀድናቸውን ዕቅዶ ከግብ ልናደርስ ይገባል ብለዋል።