በኮሪደር ልማቱ አካባቢ የሚደረግ የጽዳት ዘመቻ ህብረተሰቡ የጽዳትና የልማቱ ባለቤት ለማድረግ እንደሆነ ተገለጸ።
በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ከ6 ኪሎ -በሽሮ ሜዳ - እንጦጦ የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት የጽዳት ዘመቻ መርሃ ግብር ተካሄዷል።
በጽዳት ዘመቻው ላይ በመገኘት መልዕክታቸውን ያስተላለፉት የጉለሌ ክፍለ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መሰለ ይትባረክ በኮሪደር ልማቱ አካባቢ የሚደረግ የጽዳት ዘመቻ ህብረተሰቡን ባለቤት ከማድረግ በተጨማሪ ውብና ጽዱ አዲስ አበባን ለመፍጠር ከተያዘው እቅድ አንዱ ነው ብለዋል።
ኃላፊው አክለውም የኮሪደር ልማቱን ከቆሻሻ በመጠበቅ፤በባለቤትነት በመያዝ፣ጽዳትን ባህል በማድረግ የትኛውንም ልማት በጋራ በማከናወን በአንድነት ሆነን ለለውጥና ውጤታማነት እንሰራለን ሲሉ ተናግረዋል።
በክፍለ ከተማው ህብረተሰቡ ጽዳትን ባህል እንዲያደርግ የተለያዩ የጽዳት ንቅናቄ በማድረግ ላይ ይገኛል በዛሬው ዕለትም በኮሪደር ልማት በሚከናወንበት ህብረተሰቡ የጽዳት ባለቤትና የልማቱ ባለቤት እንዲሆን የጽዳት ዘመቻ አካሄደናል ብለዋል።
በኮሪደር ልማቱ በሚካሄድበት አካባቢ በተደረገው የጽዳት ዘመቻ የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች፣ ነዋሪዎችና እንዲሁም የጽዳት ባለሙያዎች የተሳተፉበት የፅዳት ዘመቻ የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት አካባቢ የጽዳት ዘመቻው ተካሂዷል::