የአገልግሎት አሰጣጥ በአግባቡ እና በተቀላጠፈ መልኩ አየተሰጠ ለመሆኑ የአገልግሎት ቀን ምልከታ ተደረገ ።
በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስ የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት፣ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ጨምሮ በሁሉም ተቋማት የአገልግሎት አሰጣጥ በተሻለ መልኩ እየተሰጠ ይገኛል።
በክፍለ ከተማ አስተዳደር የባለ ጉዳይ ቀንን ምክንያት በማድረግ የአገልግሎት አሰጣጥ ቀን ምልከታ ተደርጓል።
በወረዳው በባለ ጉዳይ ቀን አገልግሎት አሰጣጡን ቀልጣፋ እንዲሁም ማህበረሰቡን ለማርካት እና የተልጋዩን እንግልት ለመቀነስ የሚያስችል የተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ ተጠናክሮ ቀጥሏል።
አመራሩ ፣ባለሙያውና ባለድርሻ አካላት ባለጉዳይን በቢሮ ቁጭ ብሎ ማገልገልና ወቅቱን ጠብቆ ምላሽ መስጠት ስራ በተቀናጀ እና በተጠናከረ መልኩ እየተሰጠ ይገኛል ።