በተመጣጣኝ ዋጋ የፍጆታ ዕቃዎች የት ማግኘት ይችላሉ?

user 24-Oct-2026 ፖለቲካ

በተመጣጣኝ ዋጋ የፍጆታ ዕቃዎች የት ማግኘት ይችላሉ?

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ ነዋሪው ላይ የሚያሳድረውን ጫና ከግምት ውስጥ በማስገባት መጠነ ሰፊ ተግባራትን እያከናውን ይገኛል ።

በተለይም የዕለት ተዕለት ፍጆታዎች በመዲናዋ በሚገኙ የተለያዪ ቦታዎችና አማራጮች በቀላሉና በተመጣጠነ ዋጋ ማግኝት እንዲቻል ዘላቂ የመፍትሄ ስራዎች በመስራት ላይ ይገኛል።

በዚህም ነዋሪው የፍጆታ ምርቶችን የሚያገኙባቸው አማራጭ ቦታዎች የተቀመጡ ሲሆን ከ292 በላይ የሚሆኑ በከተማዋ ሁሉም አካባቢ የሚገኙ የሸማች ማህበራት የስጋ አቅርቦት ማዕከላት፣ የላፍቶ ቁጥር 1 እና ቁጥር 2 የገበያ ማዕከል ፣ የቦሌ ለሚ የኢንዱስትሪ እና የግብርና ምርት ማቅረብያ ማዕከል፣ የኮልፌ የግብርና ምርቶች መሸጫ የገበያ ማዕከል እንዲሁም የለሚ ሁለገብ የገበያ ማዕከል፣ የለሚ ኩራ የግብርና ምርቶች ገበያ ማዕከል፣ የአቃቂ የሰብል ምርት የገበያ ማዕከል፣ የአቃቂ የእንስሳት ልማት እና ልህቀት ማዕከል ጨምሮ የካ ጉራራ የገቢያ ማዕከል እና በ119ኙም ወረዳዎች የሚገኙ 282 የሰንበት ገበያዎች ግብይት መፈፀም ይቻላል ።

የተለያዩ ምርቶችን መሸመት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው በአቅራቢያው ወደሚገኝ ገበያ ጎራ ብሎ በተመጣጣኝ ዋጋ መሸመት ይችላል ።

Related Post

ልዩ ዜና