በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የባለጉዳይ ቀንን መሠረት በማድረግ በክፍለ ከተማው ሥር በሚገኙ ሁሉም ጽሕፈት ቤቶች የተቀናጀ የአገልግሎት አሰጣጥ እየተከናወነ ይገኛል።
ያነጋገርናቸው ተገልጋዮች እንደገለጹት ከዚህ ቀደም ይሰጥ ከነበረው አገልግሎት አንጻር በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ መሻሻል ታይቷል። በተለይም ባለሙያዎችና አመራሮች ከሕብረተሰቡ ጋር በቀጥታ በመገናኘት የሚቀርቡ የአገልግሎት ጥያቄዎችን በፍጥነት ለመፍታት እየሠሩ ያሉት ሥራ ውጤታማ መሆኑን ገልጸዋል።
ተገልጋዮቹ አክለውም የሚሰጠው አገልግሎትም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መምጣቱን በአድናቆት ገልጸዋል።
በተጨማሪም አመራሮችና ባለሙያዎች እየሰጡ ያሉት የተሻለ አገልግሎት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ተናግረዋል።
በክፍለ ከተማው የባለጉዳይ ቀንን በማስመልከት በየሳምንቱ ረቡዕና ዓርብ በክፍለ ከተማው ሥር በሚገኙ ሁሉም ጽ/ቤቶች እንዲሁም በተቀናጀ የአገልግሎት መስጫ ማዕከል አገልግሎት እየተሰጠ ይገኛል።