የጉለሌ ክፍለ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት የኮሙኒኬሽን ጽ/ቤትና የመልካም አስተዳደር ቅሬታና አቤቱታ አስተዳደር ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት የገጽ ለገጽ የእንጠያየቅ መድረክ አካሂደዋል።
በመድረኩ የክፍለ ከተማው ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ ወገሴ እንደገለጹት የመድረኩ ዓላማ የሕብረተሰቡን ጥያቄና ቅሬታ በቀጥታ በማዳመጥ ምላሽ መስጠት የአገልግሎት ጥራትን ማሻሻልና የተገልጋዮችን እርካታ ማሳደግ ነው።
የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ ቤት ኃላፊ አቶ ድሪባ ታደሰ በቀደሙት መድረኮች የተነሱ ጥያቄዎችን ለመፍታት የአገልግሎት እርካታን ለመገምገምና የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ለማሻሻል ሥራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል።
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ስርካለም ተፈሪ በበኩላቸው መድረኩ ሕዝብና መንግሥትን በማገናኘት ጥያቄዎች በቀጥታ ምላሽ እንዲያገኙና የተሰጡ ምላሾችም እንዲረጋገጡ እንደሚያግዝ አስረድተዋል።
የመልካም አስተዳደር፣ ቅሬታና አቤቱታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብርሃም ምስጋናው መድረኩ በአገልግሎት አሰጣጥ ያሉ ክፍተቶችን ለመለየትና ለማረም እንደሚያግዝ ገልጸዋል።
በመድረኩ የጤና፣ የንግድ፣ የመንግሥት ቤቶች አስተዳደር፣ የሥራና ክህሎት፣ የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት እንዲሁም ሌሎች ተቋማት ተሳትፈው ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል።