ነዋሪው ለልማት ያለው ተነሳሽት ለቀጣይ ስራዎች እንዲያበረታ ያደርጋል።
(ጉለሌ ኮሙኒኬሽን ፣ 09 -02 -2019 ዓ.ም )
በጉለሌ ክፍለ ከተማ ህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በክፍለ ከተማው ወረዳ 10 አስተዳደር ብሎክ 23 እና 24 ህብረተሰቡን በማስተባበር የትቦ ቀበራ እና የአስፓልት መንገድ ፕሮጀክት ማስጀመሪያ መርሀ ግብር ተካሂዷል።
የጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ ወገሴ በማስጀመሪያ መርሀ ግብሩ ላይ ተገኝተው ባስተላለፋት መልእክት ወረዳው በህብረተሰቡ ንቁ ተሳትፎ በርካታ መሰረተ ልማቶችን እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀው አሁን አሁን ላይ አካባቢውን የበለጠ ለማልማትና ምቹ ለማድረግ የህዝቡ ተነሳሽነት እያደገ በመምጣቱ የማንንም ድጋፍ ሳይጠይቁ መንግስትን እያገዘና በራስ አቅም ያሉ ችግሮችን በፍጥነት እየፈቱ ያለበት መንገድ ለሌሎች ሞዴል መሆን የሚችል በመሆኑ ፕሮጀክቱን በተቀመጠለት ጊዜ በማጠናቀቅ ለህብረተሰቡ ማስረከብ ያስፈልጋል ብለዋል።
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ይከበር ስማቸው በበኩላቸው ከተማችን አዲስ አበባ የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ በርካታ ሰው ተኮር የልማት ስራዎች በማከናወን ላይ ይገኛል በመሆኑም ህብረተሰቡ አካባቢውን በማስዋብ ለኑሮ ምቹ ውብና ተስማሚ በማድረግ ሞዴል አካባቢን በመፍጠር በመስራት አርዓያ የሚሆን ተግባር ማከናወን ይገባል ብለዋል።
የወረዳው ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መሰለ ይትባረክ የመንገድ ፕሮጀክቱ 1ኪ.ሜ በላይ የሚሸፍን እንደሆነ ገልጸው ማህበረሰቡን በማስተባበርና በማነሳሳት አካባቢን ማልማትና ለሌሎች ምሳሌ እንዲሆኑ በአጭር ጊዜ ለመጨረስ የታለመ ፕሮጀክት መሆኑን ገልጸዋል።
ኢንጂነር አባይነህ በበኩላቸው በህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት አስተባባሪነት የአስፓልት እና ትቦ ቀበራ የአካባቢው ማህበረሠብ እውቀቱን ሙያውንና ሀብቱን ተጠቅሞ በራስ አቅም 30 ሚሊየን ብር የሚያወጣ መንገድ እና ትቦ ቀበራ ስራ በአጭር ቀን በመጨረስ ለማህበረሰቡ የሚያስረክቡ እንደሆነ ገልጸዋል።