በጉለሌ ክፍለ ከተማ የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ጽ/ቤት ቀልጣፋ አገልግሎት ጊዜያቸውን በአግባቡ እንዲጠቀሙ እንዳስቻላቸው ተገልጋዮች ገለጹ።

user 28-Oct-2026 ልማት

የክፍለ ከተማው ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት የአገልግሎት ቀንን አስመልክቶ በክፍለ ከተማው በሚገኙ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በመዘዋወር ከተገልጋዮች ጋር ቆይታ አድርጓል።

በዚሁ ወቅት በግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ጽ/ቤት የግንባታ ፈቃዳቸውን ለማራዘም የመጡ ተገልጋዮች በተቋሙ የሚሰጠው አገልግሎት ግልጽ፣ ቀልጣፋና ውጤታማ መሆኑን ገልጸዋል።

በተለይም ባለሙያዎች ከመግቢያው ጀምሮ የት መሄድና እንዴት አገልግሎት ማግኘት እንዳለባቸው ግልጽ መረጃ እንደሚሰጧቸው ጠቁመው ይህ አሠራር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥያቄ አቅርበዋል።

ሌላኛው በጽቤቱ የግንባታ ፈቃድ ለማውጣት የመጡ ተገልጋይ የአገልግሎት አሰጣጡ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መምጣቱን ገልጸዋል።

ተገልጋዩ አክለውም አላስፈላጊ ምልልስና እንግልት ሳይገጥማቸው ለያዙት ጉዳይ ቀጥተኛ ምላሽ ማግኘት መቻላቸው እንዳስደሰታቸው ተናግረዋል።
በባለጉዳዮች ቀን አስመልክቶ የሚካሄደው የአገልግሎት አሰጣጥ ምልከታም በተጠናከረ መልኩ እንደሚቀጥል ተገልጿል

Related Post

ልዩ ዜና