የጉለሌ ክፍለ ከተማ የጸጥታ የጋራ ግብረ ሃይል መጪውን የኢሬቻ በዓል ፍጹም ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማጠናቀቁን ገለጸ።

user 30-Sep-2025 ወቅታዊ ጉዳይ

ጉለሌ ክፍለ ከተማ የጸጥታ የጋራ ግብረ ሃይል መጪውን የኢሬቻ በዓል ፍጹም ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማጠናቀቁን ገለጸ።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር የጸጥታ ጥምር ሃይል መጪውን የኢሬቻ በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ በተሰሩ የሰላምና ጸጥታ ማስጠበቅ ስራዎችና በቀጣይ የክፍለ ከተማውን የጸጥታ ሁኔታ በተጠናከረ አሰራር ማስጠበቅ በሚቻልበት ሁኔታ ዙሪያ ውይይት አድርጓል።

ውይይቱን የመሩት የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች ፣ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ ኢሬቻ በዓል በህብርብሔራዊ አንድነት ፣ በፍቅር ፣በሰላም በዪኒስኮ የተመዘገበ በመሆኑ ገቢ የሚያመንጩ አደባባይ በዓል ሰለሆኑ ባህላዊ ትውፊቱን ጠብቆ ከዚህ በፊት እንደምናከብራቸው አደባባይ በዓላት ያለምንም አንዳች ችግር ከብሎክ አመራሮችና ከጸጥታ አካለት ጋር በመቀናጀት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ ወገሴ በበኩላቸው በክፍለ ከተማ ደረጃ በተሰራው የተቀናጀ ስራ በርካታ ውጤቶች መመዝገባቸውንና ለጸጥታ ስጋት የተባሉትን ነገሮች ከጸጥታ መዋቅሩ ጋር በቅንጅት እየተሰራ ይገኛል ከአጎራባች የኦሮሚያ ከተሞች ጋር በመቀናጀት ፍተሻና አሰሳ ስራዎች ተጠናክረው በመሰራት ላይ ይገኛሉ ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ደንድር በከተማዋ የኢሬቻ በዓል ባህላዊ ትውፊቱን በጠበቀ መልኩ እንዲከር ለማድረግ የጸጥታ መዋቅሩ ከሰላም ሰራዊቱ ጋር በመናበብ የስምሪትና የመረጃ ልውውጥ ስርዓታችንን በማስተካከል ህብረተሰቡ ሰላሙን ከጸረ ሰላም ሃይሎች እንዲጠብቅ በማድረግ በዓሉ በሰላም ተከብረው እንዲጠናቀቁ ማስቻል ይገባል ብለዋል።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አቶ ሀብታሙ ደረጀ በበኩላቸው በዓሉ በሰላም እንዲከበር የጸጥታ ጥምር ሃይሉ ቅንጅታዊ ስራዎችን ለቀጣይ አጠናክሮ በመሰራትና የነበሩ ክፍተቶችን በማረምና በማስተካከል የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ በትኩረት መንቀሳቀስ ይገባል ብለዋል።

በቀጣይ የፀጥታ ኮማንድ ፖስቱ የሰላም ሰራዊቱን ማጠናከር፣ ስጋት ያለባቸው ቦታዎችን የተለየ ፣ በዓሉን በቅንጅት በመስራት ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ማድረግ እንደሚገባ ተገልጿል።

Related Post

ልዩ ዜና