ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለምክር ቤት አባላት ባለፉት 6 ወራት በከተማው በተሰሩ በርካታ ስራዎች ፤ እየተሰሩ ባሉ እና ቀጣይ የሚሰሩ ዘርፈ ብዙ ስራዎች ላይ የሰጣቸው ማብራሪያዎች፡፡

user 06-Feb-2026 ማህበራዊ ጉዳዮች

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለምክር ቤት አባላት ባለፉት 6 ወራት በከተማው በተሰሩ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ ባሉ እና ቀጣይ የሚሰሩ ዘርፈ ብዙ ስራዎች ላይ የሰጣቸው ማብራሪያዎች፡፡

በውኃ ልማት ዘርፍ በተመለከተ

👉የከተማዋን የውኃ አቅርቦት ሽፋን በበጀት ዓመቱ መጨረሻ በቀን በ60ሺህ ሜ.ኩብ የሚያሳድጉ የተለያዩ የውሃ ልማት ሥራዎች ተቀርጸው ተግባራዊ በመደረግ ላይ የሚገኙ ሲሆን ከዚህ አንጻር ፤-
👉ባለፉት 6 ወራት በቀን 37,996 ሜ.ኩብ ውሃ መስጠት የሚያስችሉ የ21 ጥልቅ ጉድጓዶች ቁፋሮ ሥራ በማጠናቀቅ በቀን 3,996 ሜ.ኩብ ውሃ መስጠት የሚያስችሉ 3 ጉድጓዶች ወደ ስርጭት ሲስተም እንዲገቡ ተደርጓል፡፡ 
👉በቀን 100ሺህ ሜ.ኩብ ውኃ ማምረት ከሚያስችለው የጭቋላ ዌል ፊልድ የውሃ ልማት ፕሮጀክት ጋር ተያይዞ የ20 ጉድጓዶች ቁፋሮ ሥራ ሙሉ በሙሉ ተጠናቅቆ ወደ ስርጭት ሲስተም ለማስገባት እየተሰራ ይገኛል፡፡ 
👉የዘመናዊ ፍሳሽ አገልግሎት ተደራሽነትን ለማሳደግ የሚያስችሉ 8 ፕሮጀክቶች በቀን 20ሺህ ሜ.ኩብ ፍሳሽ የማጣራት አቅም በመፍጠር እስከ 235ሺህ የሚደርስ የህብረተሰብ ክፍል የዘመናዊ ፍሳሽ አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡
👉የኮዬ ፈጬ የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ ግንባታ ፕሮጀክት 75% ፤በቀን 106ሺህ ሜ.ኩብ ፍሳሽ የማጣራት አቅም የሚኖረው የምሰራቅ ተፋሰስ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ ግንባታ 30% ማድረስ ተችሏል፡፡
👉በሌላ በኩል 20.02 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ ከመኖርያ ቤቶች የሚፈጠረውን ፍሳሽ ቆሻሻ በመስመር እና በተሸከርካሪ በማሰባሰብ 19.73 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ ፍሳሽ ቆሻሻ ማስወገድ ተችሏል፡፡
        የቤት ልማት አቅርቦትን በተመለከተ

ü  በመንግስት በጀት እና በበጎ አድራጎት 11,550 መኖሪያ እና 707 ንግድ ቤቶች በድምሩ 12,257 መኖሪያ እና ንግድ ቤቶችን ለልማት ተነሺዎች፣ ለአገር ባለውለታዎች፣በጨረታና በመልካም አስተዳደር ማስተላለፍ ተችሏል፡፡  

ü  በመንግስትና የግል አጋርነት እና በከተማው በጀት ሊገነቡ ከታቀዱ 100 ሺ ቤቶች ላይ 97,000 ቤቶች ወደ ግንባታ ሂደት የገቡ ሲሆን ሁሉንም በተያዘላቸው ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ እየሰራን ነው፡፡ 

ü  በግል እና ሪል ስቴት የተገነቡ ቤቶች 13,517 ሲሆን በኮሪደር የለሙ 810 የንግድ ቤቶችን በልማት ለተነሱ አነስተኛ ነጋዴዎች ተላልፏል፡፡

ü  በመንግስት እና በግል አጋርነት በተሰራው ዘርፈ ብዙ ስራ ከ70 በላይ ፕሮጀክቶችን ወደ ሥራ ማስገባት ተችሏል፡፡ በዚህም ከብር 1.3 ትሪሊዮን በላይ ካፒታል ኢንቨስትመንት መሳብ ተችሏል፡፡

ü  በ65 ህብረት ሥራ ማህበራት ለተደራጁ 5,110 ቤት ገንቢዎች ጠንካራ ድጋፍ በመደረጉ 42 ማህበራት ወደ ግንባታ ምዕራፍ ተሸጋግረዋል::

ü  ከለውጡ ወዲህ 45,566 ቤቶች የተገነቡ ሲሆን በዚህ 6 ወር ደግሞ 4,990 ቤቶች ተገንብተዋል፡፡ 

ü  ባለፉት 6 ወራት ብቻ 1.5 ቢሊየን ብር በመሰብሰብ ለባንክ ተመላሽ በማድረግ የቦንድ ብድር ጫናን መቀነስ የተቻለ ሲሆን በአጠቃላይ ከለውጡ በፊት ለጋራ መኖሪያ ቤቶች መገንቢያ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከተወሰደው የቦንድ ብድር ከወለዱ ብር 61.2 ቢሊየን ከለውጡ ወዲህ መክፈል ተችሏል፡፡
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Related Post

ልዩ ዜና