የጉለሌ ክፍለ ከተማ ህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ከጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ጋር በጋራ በመሆን የ2018 ዓ.ም የበጋ በጎ ፈቃድ የቤት እድሳት መርሃ ግብር በወረዳ 9 አካሄደ ።
በመርሃ ግብሩ ላይ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ጽ/ቤት አቶ ሚኪያስ ቦንኬ እንደተናገሩት የ2018 የበጋ በጎ ፈቃድ መርሃ ግብሮች ሰው ተኮር የሆኑ ሰፋፊ ተግባራትን የሚከናወንበት እንደሆነ ገልጸው በበጋ በጎ ፈቃድ ፕሮግራም የህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ የፋይናንስ አስተዳደር ፑል ኃላፊ አቶ ደረጀ ክንፈ በበኩላቸው ጽ/ቤቱ ከሚያከናውናቸው መደበኛ ተግባር በተጨማሪ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት በበጋ በጎ ፈቃድ ተግባር አንዱ የሆነው የአቅመ ደካማ ቤት እድሳት ነው በዛሬው ዕለት በወረዳ 9 ዕድሳት አስጀምረናል ብለዋል።