የጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት 13ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባዔ ላይ የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎችን በዝርዝር ቀርቧል።

user 10-Feb-2026 ማህበራዊ ጉዳዮች

የጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት 13ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባዔ ላይ የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎችን በዝርዝር ቀርቧል። 
የክፍለ ከተማው አስተዳደር  ባለፉት ስድስት ወራት  በነቃ የነዋሪዎች የልማት ተሳትፎ እና የጋራ ድጋፍ የተመዘገቡ  አበረታች ውጤቶችን  በማጠናከር የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን አስቀምጧል። 
👉የከተማ ግብርና ፣የሸማቾች እና የንግድ   ተቋማትን አቅም በማጠናከር ኑሮ ውድነትን በልዩ ትኩረት ማረጋገጥ 
👉 በዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ሌብነትና ብልሹ አሰራር በመከላከል የአገልግሎት አሰጣጥን ማሻሻል
👉 የጉለሌ  ልዩ መለያ የሸማና የሸክላ የእደጥበብ  ጥበብ ውጤቶችን በስፋት በማስተዋወቅ ክፍለ  ከተማችን የቱሪስት መስብ ማድረግ
👉 የትምህርት ጥራትና  ተደራሽነትን  ለማሳደግ የተማሪዎች የምገባ  ማስፋፊያ  ግንባታ  ማጠናከር 
👉 የመስሪያ  ቦታዎችን ግንባታና  አቅርቦትን በማጠናከር አስተማማኝና ፍትሃዊ የወጣቶች የስራ  ዕድል  ፈጠራ ማረጋገጥ በትኩረት መስራት 
👉 የህብረተሰቡን ግንዛቤ በማሳደግ የተሰሩ የልማት ስራዎችን በባለቤትነት ተከታትሎ በመጠበቅ  አጋዥ  አድርጎ መስራት። 
👉በክፍለ ከተማው የራሱ መለያ የሚገልጽ የህዝብ  ፓርክ መገንባት  
👉 ከህብረተሰቡ የሚነሱ የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በቁርጠኝነት በመፍታትና የነዋሪዎቻችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በቀጣይ ትኩረት የሚሰጥባቸው  ዋና ዋና ተግባራት መሆናቸዉን የጉለሌ  ክፍለ  ከተማ ዋና ስራ  አስፈፃሚ አቶ ወልዴ ወገሴ  አብራርተዋል።

Related Post

ልዩ ዜና