በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የ2017 የማጠቃለያ ፈተና ከወሰዱ የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች መካከል 95.3% ተማሪዎች በማሳለፍ በከተማ ደረጃ 2ኛ ደረጃ መውጣት መቻሉን ተገለፀ።

user 25-Jun-2025 ልማት

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሚሊዮን ኮራ እንደተናገሩት ከሰኔ 03-04/2017 ዓ.ም በተሰጠው ከተማ አቀፍ የ8ኛ ክፍል የመካከለኛ ደረጃ መልቀቂያ ሰርተፊኬት ፈተና በጉለሌ ክ/ከተማ ከተፈተኑት 4828 ተማሪዎች መካከል 4600 ተማሪዎች 50% እና ከዚያ በላይ በማምጣት ወደ 9ኛ ክፍል የተዛወሩ ሲሆን; ክ/ከተማችን 95.3% በማሳለፍ በከተማ ደረጃ *2ኛ* በመውጣት የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ ተችሏል።

ሀላፊው አክለውም ይህ ዉጤት በ2016 ከነበረዉ 87 % የመጠነ ማሳለፍ ወደ 95.3 % ማደግ መቻሉን ገልጸው የዉጤቱ መሻሻል ዋንኛ ምክንያትም የከተማ እና የክ/ከተማ አስተዳደሩ ለትምህርት ሴክተሩ የሰጠዉ ትኩረት ፤ መንግስት ለተማሪዎች እያደረገ ያለዉ የግብአት አቅርቦት እና የምገባ ፕሮግራም ትልቅ ኢንቨስትመንት ፤ በትምህርት ቤቶችና አከባቢዎች ለመማር ማስተማሩ ምቹ እንዲሆኑ እየተሰራ ያለዉ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራ በተለይም በትምህርት ለትዉልድ መረሃ ግብር እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ተጠቃሽ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

በመሆኑም ይህ ውጤት እንዲመጣ የበኩላቸውን ድርሻ ለተወጡ የክ/ከተማዉ ከፍተኛ አመራሮች፣ ወረዳ አመራሮች፣የት/ት አመራሮችና በለሙያዎች ፣መምህራኖች፣ ወላጆች እና ተማሪዎች የግል ጥረታቸዉ ሲያደርጉ የነበረ በመሆኑ ጭምር መሆኑን ገልጸው ምስጋና አቅርበዋል።

Related Post

ልዩ ዜና